አራት ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ከ23 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን ይመራሉ።

ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የአፍሪካ ከ23 አመት በታች የማጣሪያ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአህጉሪቱ ሀገራት ይካፈላሉ። ህዳር 2/2019 ኢስዋቲኒ በሜዳዋ አልጄሪያን የምትገጥምበትን ጨዋታ ኢትዮጵያን አራት ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲመሩ በካፍ ተመርጠዋል።
ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ወጣቱ ሀይማኖት አዳነ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ትግል ግዛው እና አማን ሞላ በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ማኑሄ ወልደፃዲቅ መመደባቸው ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ