መነሻ ገጽ ከ 17 ዓመት በታች ከ17 አመት በታች ስትራቴጂ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደረገ
ከ 17 ዓመት በታችዜናዎች

ከ17 አመት በታች ስትራቴጂ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደረገ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የታዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂን ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ላለፉት ዓመታት በፓይለት ፕሮጀክት ፣ በክልል እንዲሁም ሀገር አቀፍ የምልመላ እና የመረጣ ሂደትን አጠናቆ ፣ የታዳጊ እግር ኳስን በተሻለ መዋቅራዊ ለውጥ ማስቀጠል የሚያስችልን ከ17 አመት በታች ስትራቴጂ እና ሀገር አቀፍ ውድድርን ማዘጋጀቱን በጁፒተር ሆቴል ከክልል ፌድሬሽኖች እና የስፖርት ቢሮዎች ጋር ስምምነት ባደረገበት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ወጣቶች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂ በቀላል ሆኖም በጠንካራ መነሻ ሃሳብ ላይ የተገነባ ሀገር አቀፍ የተጫዋቾቸ ማሳደጊያ እንደሆነም ተነግሯል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ፌዴሬሽኑ የታዳጊዎች ልማት ላይ ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ሀላፊነት ቢሰጥም ሁለት ክልሎች ብቻ የሙከራውን አካሄድ መተገበራቸው በዕለቱ ተጠቅሷል። ይህም ባለፈው ዓመት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በታዳጊዎች ልማት ላይ ለመስራት ከስምምነት ቢደርሱም ተግባር ድክመቶች ታይተዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንደ ሀገር እየተማረ የሚጫወት ታዳጊ ለማፍራት በሙከራ ላይ የነበረውን ሂደት ወደ ዘላቂ አካሄድ ለመቀየር መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽኑ የህክምና ክፍል ሀላፊ እና የስትራቴጂክ ዕቅድ አማካሪው ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ በበኩላቸው ስትራቴጂው በተመረጡ 21 ከተሞች በሚተገበር ከ17 ዓመት በታች ሊግ እንደሚካሄድ ገልፀዋል። በየከተሞቹ ከ16 እስከ 20 የሚደርሱ ክለቦች በደርሶ መልስ እንዲወዳደሩ እንደሚደረግም ይፋ ተደርጓል። ፌዴሬሽኑ በየከተሞቹ የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያዎችን የሚመድብ ሲሆን ፣ የከተማ የማዕከል እና የሀገር አቀፍ ምልመላ (ካምፕ) እንዲሁም ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራት ላይም በትልቁ እንደሚሠራ ገልፀዋል።

በታዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂው መሠረት የውድድር መዋቅሩ በአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ መሠረት ያደረገ እንደሚሆን እና በአንድ ዓመት 105 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግበትም ይፋ ሆኗል።

በመጨረሻም በያዝነው አመት በሚጀምረው ከ17 አመት በታች ድልድል በማዕከል ተከፍሎ ይህንን ይመስላል።

ሰሜን ኮንፈረንስ

ባህርዳር ከተማ ፣ መቐለ ፤ ሰመራ ከተማ ፣ ጎንደር ከተማ እና ደሴ ከተማ

ምዕራብ ኮንፈረንስ

ጅማ ከተማ ፣ ቦንጋ ከተማ ፣ ጋምቤላ ከተማ እና አሶሳ ከተማ

ምሥራቅ ኮንፈረንስ

ድሬዳዋ ከተማ ፣ ሐረር ከተማ እና ጅጅጋ ከተማ

ማዕከላዊ ኮንፈረንስ

አዲስ አበባ ከተማ ፣ አዳማ ከተማ ፣ አምቦ ከተማ ፣ ሆሳዕና ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ

ደቡብ ኮንፈረንስ

ሀዋሳ ከተማ ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ፣ አርባ ምንጭ ከተማ እና ሮቤ ከተማ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...