ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከ ያንግ አፍሪካ እና አዛም ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ወደ ታንዛኒያ አምርተዋል።
በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዲዮ ሚሉቲን ሚቾ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቢሾፍቱ ከተማ በይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ልምምዳቸውን ሲሰሩ ከርመው ባሮ ከሚባል የጋምቤላ ቡድን እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ካደረጋጓቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ ከሰአት 34 የሉካን ቡድን አባላት በመያዝ ወደ ዳሬሰላም አምርተዋል ። በዳሬሰላም ቆይታቸው ከሀገሪቱ ሀያል ክለቦች ያንግ አፍሪካ እና አዛም ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን የሚያደርጉ ይሆናል።

አስተያየት ይስጡ