ያለፉትን ሁለት አመታት በክትፎዎቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ እና ከዚህ ቀደም ለሲዳማ ቡና መጫወት የቻለዉ የመሐል ተከላካዩ ዳግም ንጉሴ ሁለት አመት በሚቆይ የስምምነት ዉል ለሀድያ ሆሳዕና ለመጫወት ፊርማዉን አኑሯል።
በተጨማሪም ክለቡን በተጠናቀቀው የዉድድር አመት አጋማሽ የተቀላቀለዉ እና በመሐል ተከላካይነት የሚጫወተዉ ግርማ በቀለ ተጨማሪ አመታትን በክለቡ የሚያቆየውን ወል ፈርሟል።
በተያያዘም ከአሰልጣኙ ሙልጌታ ምህረት ጋር ዉዝግብ ዉስጥ የሚገኘዉ ሀድያ ሆሳዕና በቀጣይ ቀናትም በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እንደሚቀላቀሉ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
አስተያየት ይስጡ