አራት አሰልጣኞችን ያወዳደረው ኢትዮጵያ መድን በመጨረሻም ደጉ ዱባሞን መረጠ።
አሰልጣኝ ለመቅጠር አራት አሰልጣኞችን ማለትም ገብረክርስቶስ ቢራራ ፣ ካሊድ መሐመድ ፣ ታዬ ናኒቻን እና ደጉ ዱባሞን ለአንድ ሳምንት ሲያወዳድር ከቆየ በኋላ በመጨረሻም ክለቡ አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞን በቦታው ሾሟል።

የቀድሞው የመተሐራ ስኳር እና ሀምበሪቾ ዱራሜ ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም በአዳማ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በተጠናቀቀው አመት የወላይታ ድቻ ረዳት አሰልጣኝ የነበሩትን አሰልጣኝ ዱባሞን አዲሱ አሰልጣኝ ማድረጉን ክለቡ ያደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።
አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ሀምበሪቾ ዱራሜን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማሳደጉ ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ