ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳዲስ ተጫዋቾችን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።

ለቀጣዩ የውድድር ዘመን በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊት ሚቾ እንደሚመሩ የሚጠበቁት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አማካዩ ብሩክ በላቸውን ተጨማሪ አዲስ ፈራሚ ማድረግ ችለዋል። በሶዶ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ከ20 አመት በታች ቡድን ከተገኘ በኋላ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ የተሰጠውን የሙከራ ዕድል በአግባቡ በመጠቀም በኢትዮጵያ መድን መለያ በሊጉ የተመለከትነው ተጫዋቹ ቀጣዩ መዳረሻው የፈረሰኞቹ ቤት መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ