ከወልዋሎ ጋር የኢትዮጵያ ዋንጫን ያነሳው ግብ ጠባቂ እና ከአንድ አመት በፊት ለፋሲል ከነማ የተጫወተው አጥቂ ለሀገራቸው ክለብ ፈርመዋል።
ከወልዋሎ አዲግራት ጋር በግሉ ጥሩ የውድድር ዘመን ያሳለፈው እና ከክለቡ ጋር የኢትዮጵያ ዋንጫን ያነሳው የግብ ዘቡ ጆኤል ሙታክብዋ እና የቀድሞው የፋሲል ከነማ አጥቂ ማርቲን ኪይዛ የሀገራቸው ዩጋንዳ ክለብ የሆነውን ኪታራን መቀላቀል ችለዋል።

ለሀገሩ ክለቦች ኤክስፕረስ ፣ ኩዌቱሜ ፣ ኢንቴቤ እና ቡል ከተጫወተው የግብ ዘቡ እና የሀገሩን ክለብ ቫይፐርስን ለቆ ከአመት በፊት ለፋሲል ከነማ የተጫወተው አጥቂው የነበረውን ከሱዳኑ ኤል ሜሪክ ክለብ በተመሳሳይ አንድ አመት ፊርማቸውን አኑረዋል።
አስተያየት ይስጡ