ባህርዳር ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አደሰ
በዝውውሩ በነቃ መልኩ እየተሳተፈ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ ቀደም ባለው ዘገባዬ የበረከት ጥጋቡን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘም መቻሉን የጠቆምኩ ሲሆን አሁን ደግሞ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል።
የቀድሞው የልደታ ክፍለ ከተማ ፣ ሱሉልታ ከተማ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በድጋሚ ተመልሶ በባህርዳር ከተማ እየጫወተ የሚገኘው የመሐል ተከላካዩ ወንድሜነህ ደረጀ እና ባህርዳር ከተማን ከታችኛው የሊግ ዕርከን ያሳደገው የቀድሞው የመቻል እና የባህርዳር ከተማ ባለውለታ የመስመር ተከላካዩ ግርማ ዲሳሳ ውሉን በጣና ሞገዶቹ ቤት አራዝመዋል።
አስተያየት ይስጡ