ፍፁም ጥላሁን የንግድ ባንክ ሦስተኛው ፈራሚ ሆኗል
በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች እስከ አሁን ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ጨምሮ የስድስት ነባሮችን ፊርማ ያገኘ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ልጅነት ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተመለሰ በኋላ አስደናቂ የውድድር ዘመናትን በተለይ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ማሳየት የቻለው የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ አጥቂ የሆነው ፍፁም ጥላሁን ከፈረሰኞቹ ጋር አለመቀጠሉን ተከትሎ ከአራት የሊጉ ክለቦች ጋር ካደረገው ድርድር በኋላ ቀጣይ ማረፊያው ንግድ ባንክ መሆኑ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ