ባህርዳር ከተማ የወሳኝ አጥቂውን ውል አራዝሟል
በዝውውሩ በነቃ መልኩ መሳተፋቸውን የቀጠሉት ባህርዳር ከተማዎች የአጥቂያቸውን ወንድወሰን በለጠን ውል ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን አረጋግጫለሁ።
የቀድሞው የአውስኮድ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በ2016 የውድድር ዘመን ጥር ወር ላይ ከከፍተኛ ሊጉ ባቱ ከተማ ለባህርዳር ከተማ በመፈረም ሰላሳ ወራቶችን በክለቡ ያሳለፈ ሲሆን ለቀጣዮቹ ሁለት አመታትም ክለቡን ለማገልገል ውሉን ማራዘሙን ለማወቅ ችያለሁ።
አስተያየት ይስጡ