ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ተጫዋቾች ሲያስፈርም ሁለት ተጨማሪ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ አማካዩ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በያዝነው አመት በወልዋሎ ያሳለፈውን አማካዩ ብሩክ እንዳለን እና ከሀድያ ሆሳዕና ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ድረስ ስድስት አመታትን ያሳለፈው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ተመስገን ብርሀኑ (በረሮን) በሁለት አመት ውል አስፈርሟል!

ክለቡ በቀጣይ የወቅቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራን እና የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ ካሳዬን ከኢትዮጵያ መድን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል።
አስተያየት ይስጡ