አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ማረፊያቸው ታውቋል።
ለቀጣዩ የውድድር ዘመን አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን ለማስቀጠል አልያም ደግሞ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ጥረት ሲያደርግ የነበረው የመቻል ቦርድ በመጨረሻም አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በሁለት አመት ውል የግሉ አዶርጓል።

የቀድሞው የአዳማ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ፣ የሱዳኑ አልሀሊ ሸንዲ ፣ በላይቬሪያው ሊከርስ እና በመጨረሻም በደቡብ ሱዳኑ ጃሙስ ቆይታ የነበራቸው አሰልጣኙ በይፋ መቻል በሁለት አመት ውል ተቀላቅለዋል።
አስተያየት ይስጡ