በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከሳምንታት በፊት የተስማሟቸውን ሁለት የግብ ዘቦች በይፋ የግላቸው አድርገዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫን በማሸነፍ ዓመቱን የጀመሩት የአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኙ ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊሶች በትላንትናው ዕለት ባለ ልምዶቹን አሚኑ ነስሩ እና ብርሀኑ አሻሞን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ከሳምንታት በፊት የተስማሟቸውን ሁለት ግብ ጠባቂዎች በይፋ አስፈርመዋል።
ፋሩክ ሺካሎ ከፓትሪክ ማታሲ ቀጥሎ ሁለተኛው ኬኒያዊ ግብ ጠባቂ ሆኖ ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። ለስምንት የሀገሩ ክለቦች የተጫወተው ኤ ኤሲቢን ለቆ ኢትዮጵያ መዳረሻውን ያደረገው ሜትር ከሰማንያ አምስት የሚረዝመዝ ተጫዋቹ ያንጋ አፍሪካን ጨምሮ ለሦስት የታንዛኒያ ክለቦችም መጫወት ችሏል። ሌላኛው ከወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የተገኘው እና በጉለሌ ክፍለ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ የተጫወተው ኮክ ኩዌትም ሌላኛው ለቡድኑ የፈረመው ግብ ጠባቂ ሆኗል።



