ሸገር ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች የግሉ አደረገ።
በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ተሳትፎን ማድረግ የቻለው ሸገር ከተማ በዛሬው ዕለት ዝውውሩን በመቀላቀል ፉአድ ፈረጃን ሲያስፈርም ጋናዊውን የግብ ዘብ ሪችሞንድ አዬን ለማስፈረም የተስማማ ሲሆን ሌላኛው አዲስ ፈራሚ ተከላካዩ ብሩክ ባይሳ ሆኗል።

የቀድሞው የነቀምት ከተማ የአማካይ ተከላካይ እና መሐል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች በትውልድ ከተማው ያለፉትን ሁለት አመታት ካሳለፈ በኋላ ቀጣይ መዳረሻው ሸገር ከተማ መሆኑ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ