ሸገር ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገብተዋል።
አሰልጣኝ ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን ለቀጣዩ የውድድር አመት እንዲቀጥሉ ማድረግ የቻለው ሸገር ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን በይፋ ወደ ስብስቡ መቀላቀሉን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።
ጋናዊው ግብ ጠባቂ ሪችሞንድ አዬ ሸገር ከተማን መቀላቀል ችሏል። ለሀገሩ ክለቦች ዋፋ ፣ ህርትስ ኦፍ እና ዲሪምስ በተባሉ ክለቦች ቆይታን ያደረገው 1:89 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው የግብ ዘቡ ከምድረገነት ሽረ ጋር የተጠናቀቀውን አመት ካሳለፈ በኋላ ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ ክለቡ ሸገር ሆኗል።

ፉዓድ ፈረጃም በይፋ በዛሬው ዕለት የሸገር ከተማ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል። ከአዳማ ከተማ እግር ኳስን ከጀመረ በኋላ በሰበታ ከተማ ፣ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም የሊጉን ዋንጫ ካሳከበት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኋላ አራተኛው የእግር ኳስ ህይወቱ ክለብ ከጉዳት መልስ ሸገር ከተማ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ