የኢንስ.አብርሃምና የሰበታ ከተማ የፊርማ ስምምነት መርሃ ግብር ተካሂዷል

 

የክለቡ ፕሬዝዳንትና የሰበታ ከተማ ስፖርት ሃላፊ አቶ ቶሎሳ ዳባ እንደተናገሩት “ወደለምለሚቷና የኢንዱስትሪ ከተማ ወደሆነችው ሰበታ እንኳን ደህና መጣችሁ ክለቡ ዝግጅት አለመጀመሩ ይታወቃልና በፍጥነት ወደ ዝግጅት መዞር አለብን..ይሄ ሃላፊነት ለኢንስትራክተር አብርሃም እንደ ስራ ዕድል የሚመጥን አይደለም ምክንያቱም ታሪካቸው በሀገርና ከሀገር ውጪ የደመቀ ታሪክ ያለው መሆኑ ይታወቃል፡፡ አሁንም ባለው ሃላፊነት ተተኪ ላይ መሰራት አለበት… ፋይናንሱን ማስተካከል ወጪ መቀነስና ገቢ ማጠናከር ይጠበቃል…አሸናፊነት ጥበብ ነው ዕውቀት ነው ታሪክ መስራት ይጠበቃል ለድል ልንንቀሳቀስ የግድ ነው ለኢንስ..አብርሃም መልካም የስራ ዘመን እመኛለሁ” ብለዋል፡፡

ክለቡ ወደ ሃላፊነቱ እንድመጣ ለጣለብኝ እምነት አመሠግናለሁ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ተጨዋች አሰልጣኝ ደጋፊ በጋራ ከቆሙ ሰበታን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል ይህን ትልቅ ክለብ የሊጉ ተፎካካሪ ለማድረግ እጥራለሁ የአሰልጣኙ ቡድን አባላት ያሰለጠንኳቸው ስልጠና ስሰጥም ጥሩ ዲሲፕሊን የነበራቸው በመሆኑ ትልቅ ሞራል ሆኖኛል የክለበለ ደጋፊዎችም ለሰጣችሁኝ ድጋፍ አመሠግናለሁ ለክለቡ አቅሜ የፈቀደውን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ” ኢንስ.አብርሃም መብራቱ

የከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ

“ዛሬ የተገናኘው ከኢንስ.አብርሃም መብራቱ ስፖርት ሰላምና ልማት ነው ባለሀብቶች ከጎናችን እንዲሆኑ ሰፊ የህዝብ ድጋፍ እንዲኖረው አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ለወራት አሰልጣኝ አልነበረንም ኢንስ.አብርሃም መምጣት እንደሚችል ስንሰማ በአንድ ድምጽ ነው የወሰነው…
አሰልጣኝ አብርሃም በዲሲፕሊን የማይታማ ክለባችን ላይ ለውጥ የሚያመጣ የውጪና የሀገር ልምድ ያለው የአሰልጣኝ ቡድኑና ተጨዋቾችን ወደውጤት የሚያመጣ መሆኑን እናምናለን የከተማ አስተዳደሩ ከጎኑ ነው መልካም የስራ ዘመን ይሁን”

የደጋፊ ማህበር ፕሬዝዳንት

” አሰልጣኙ እንደሚመጣ ሲሰማ ጎል የተቆጠረ ያህል ነው ያጨበጨብነው በሹመቱ ደስተኞች ነን አሰልጣኙ ባላቸው አቅም እንተማመናለን አሁን ግን ኢንስ.አብርሃም ከታዳጊ ቡድኑ ተጨዋቾችን ከማሳደግ አንጻር ጥሩ ስራ ተሠርቶ ከፍተኛ ሂሳብ ቅነሳ ያካሂዳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ማንም ሳያውቅ የስፖርት መሠረት ያለው አዛውንቶች ወጥተው የሚደግፉት ቡድን በመሆኑ ይህን ቡድን ሲያሰለጥኑ ሙሉ የደጋፊ ድጋፍ እንዳለ ለመግለጽ እወዳለሁ ፈተናዎችንም አብረን እንደምናልፈውም ተስፋ አደርጋለሁ”

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ለአንድ አመት የክለቡ ዋና አሰልጣኝ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport