መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ በረከት ሳሙኤል ለሰበታ ከተማ መልቀቂያ አስገብቷል
ሰበታ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

በረከት ሳሙኤል ለሰበታ ከተማ መልቀቂያ አስገብቷል

አጋራ
አጋራ

የሰበታ ከተማ ተጫዋቾች የዕረፍት ጊዜያቸውን አጠናቀው ለሁለተኛ ዙር ዝግጅት እንዲጀምሩ ከክለቡ ጥሪ ቢደረግላቸውም ከደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ ልምምድ ለመጀመር ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ከሳምንት በፊት መዘገባችን ይታወሳል ።

አሁን ደግሞ የመሀል ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል ከሰበታ ከተማ ጋር ለመለያየት የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቱ ተሰምቷል ። ተጫዋቹ በደብዳቤው እንደገለፀው ከሆነ በቤተሰቡ ላይ ያጋጠመው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከክለቡ ጋር ለመለያየት ጥያቄ እንዲያቀርብ አድርጎታል ።

በረከት በመጀመሪያው ዙር ሰበታ ከተማ ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች በ11 ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን ሁለት ግቦችንም በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሎ ነበር ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...