የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እየተመራ በመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ካደረጋቸው አስራ አምስት ጨዋታዎች በአንዱ አሸንፎ በስድስት አቻ ተለያይቶ እንዲሁም በስምንት ጨዋታዎች ተሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ መቀመጡ ይታወቃል ።
ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ስሙ ይነሳ የነበረው ይህ ክለብ በህዳር 24 / 2014 ዓ.ም ከአስር የክለቡ ተጫዋቾች ከደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ቀርቦበት ነበር ። ክለቡ ከእረፍት መልስ ለሁለተኛው ዙር ዝግጅት ለማድረግ በትላንትናው ዕለት የተሰባሰበ ቢሆንም ተጫዋቾቹ ልምምድ ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ዝግጅታቸውን መጀመር ሳይችሉ ቀርተዋል ለዚህም እንደ ምክንያት የቀረበው አስራ አንድ ተጫዋቾች የ2013 ዓ.ም የአራት ወራት የደመወዝ እና የጥቅማ ጥቅም ክፍያ እንዲሁም በያዝነዉ የውድድር አመት ደግሞ ለሁሉም የክለቡ ተጫዋቾች የሁለት ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው ወደ ሶስተኛው ወር መቃረባቸው ነው ።
የ2013 የውድድር አመት ቀሪ ክፍቻዎች ያልተከፈላቸው እራ አንደለ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስገቡት ሲሆን በቅሬታ ደብዳቤያቸው ላይ እንደገለፁት ከሆነም ክፍያዎችን በተገቢው ጊዜ ባለማግኘታቸው ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል ። ስለሆነም ክለቡ ክፍያቸውን ፈፅሞላቸው ሙሉ ትኩረታቸውን በእግር ኳሱ ላይ እንዲያደርጉ እና ቤተሰቦቻቸውም ከገጠማቸው ችግር ማላቀቅ ይችሉ ዘንድ ጠይቀዋል ።

አስተያየት ይስጡ