በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘዉ መከላከያ በዛሬው ዕለት ደግሞ ወሳኝ የፊት መስመር አጥቂ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለሀዋሳ ከተማ ፣ ሰበታ ከተማ እንዲሁም ወሌቂጤ ከተማ መጫወት የቻለዉ ግዙፉ አጥቂ እስራኤል እሸቱ (ካቻ) እና በክረምቱ የዝዉዉር መስኮት ረጅም አመታትን ከቆየበት ቅዱስ ጊይርጊስ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ አዳማ ከተማ አምርቶ የነበረዉ ምንተስኖት አዳነ በዛሬዉ ዕለት ለአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቡድን መከላከያ ለአንድ አመት ከግማሽ ለመጫወት ፊርማቸዉን ማኖራቸዉ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ