መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት የዋናው እግርኳስ ቡድን ተጫዋቾቹን አግዷል….
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት የዋናው እግርኳስ ቡድን ተጫዋቾቹን አግዷል….

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርስ ስፖርት ማህበር በ2013 ዓ.ም በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው ቡድናችን ውጤታማ እንዲሆን የስራ አመራር ቦርዱ ባለው አቅም ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ቡድኑ እየተደረገለት ካለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አንጻር የሚጠበቅበትን ያህል አርኪ የሚባል እንቅስቃሴዎችን እያደረገ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት ጊዜ ደግሞ አልፎ አልፎ በቡድኑ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ተጫዋቾቻችን የሚያሳዩት ያልተገባ ባህሪና የስነ-ምግባር ጉድለት እጅጉን የሚያስቆጭ ነው፡፡

ትናንት ቡድናችን በድሬዳዋ ስታዲየም ከጅማ አባጅፋር ጋር ካካሄደው የ20ኛ ሳምንት ጨዋታ በኃላ ጌታነህ ከበደ፣ አስቻለው ታመነ፣ ጋዲሳ መብራቴ እና ሙሉዓለም መስፍን ከፍተኛ የዲሲፒሊን ግድፈት ፈጽመዋል፡፡

አብዛኞቹ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ቡድኑ በባህርዳር በነበረው ቆይታም የስነ ምግባር ጉድለት ፈጽመው የነበረ ቢሆንም አጠቃላይ ለቡድኑ ውጤታማነትና አንድነት ሲባል በማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ተደርጎ ነበር፡፡

የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ተጫዋቾቹ በፈጸሟቸው የዲስፕሊን ግድፈቶች ዙሪያ የቡድን መሪው በተፈጸመው የሥነ ምግባር ጉድለት ዙሪያ በዝርዝር በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ቦርዱ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ለጊዜው ከቡድኑ ታግደው እንዲቆዩ ተወስኗል፡፡

ስለሆነም አራቱም ተጫዋቾች ከድሬዳዋ በዛሬው እለት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

Source- SA George

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...