የኳታር የአለም ዋንጫ በቀጣይ አመት ከህዳር 12 እስከ ታህሳስ 9 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን በዳኝነት በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉት ውስጥ ስምንቱ ከአፍሪካ መሆናቸውን የአለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል ( FIFA ) ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ በዝርዝሩ ውሰጥ ከተካተቱት ዳኞች አንዱ መሆን ችሏል ።
ከባምላክ በተጨማሪም በአለም ዋንጫው ላይ የሚዳኙ አፍሪካውያን የሚከተሉት ናቸው
ሙስጠፋ ጎርባል ( አልጄሪያ )
ሬዱያኔ ጅያድ ( ሞሮኮ )
ፓፓ ባካሪ ጋሳማ ( ጋምቢያ )
ቪክተር ጎሜዝ ( ደቡብ አፍሪካ )
ጃኒ ሲካዝዌ ( ዛምቢያ )
ማጉኤቴ ንዲያዬ ( ሴኔጋል )
ጃኩኤስ ንዳላ ( ኮንጎ )
ባምላክ ተሰማ በ2018 የሩስያ አለም ዋንጫ ላይ በአራተኛ ዳኝነት አገልግሎ የተመለሰ ሲሆን በቅርቡ በካሜሩን አዘጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሴኔጋል እና ቡርኪናፋሶን የግማሽ ፍፃሜን ጨዋታ ያጫወተ ሲሆን ከቀናት በፊትም ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ባማኮ ላይ ማሊ ከቱኒዚያ ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት መምራት ችሎ ነበር ።
አስተያየት ይስጡ