By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: Qatar 2022 | የምንጊዜም ምርጡን የአለም ዋንጫ ያስመለክተን ይሆን?
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
ዜናዎች ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

Qatar 2022 | የምንጊዜም ምርጡን የአለም ዋንጫ ያስመለክተን ይሆን?

hatricksport team
hatricksport team 9 years ago
Share
SHARE

 

​ኃይለ እግዚአብሔር አድሐኖም 
ልዩ ጥንቅር ለሀትሪክ ስፖርት

 by haileegziabher adhanom @haileadhanom  

አለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) 
ከኳታር ስፖርት ኮሚቴ (QSC) ጋር በመተባበር 
ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ ኤዥያ እና አሜሪካ አህጉራት፤ 
ከ11 ሀገራት ለተውጣጡ 12 ወጣት የስፖርት 
ጋዜጠኞች በኳታር ዶሀ በስፖርት ጋዜጠኝነት እና 
አለም አቀፋዊ አሰራሩ ዙሪያ ከሚያዚያ 20 – 29/2009 
ዓ.ም ስልጠና ሰጥቷል፡፡በዚህ ስልጠና ላይ ተካፋይ 
ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ እንደ መሆኔና 
በቆይታዬ በተፈጠረልኝ ልዩ የጉብኝት አጋጣሚ፤ኳታር 
ለስፖርቱ ዘርፍ የሰጠችውን ልዩ ትኩረት እና ካላት 
ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አቅም በመነጨ ሀገሪቱ ውስጥ 
እየተከናወኑ ካሉ በርካታ ግዙፍ የስፖርት ልማት 
ስራዎች አንዱና ዋነኛየሆነውን የኳታር 2022 የአለም 
ዋንጫ ዝግጅትን በተመለከተ በተከታዩ ጽሁፌ በመጠኑ 
ላስቃኛችሁ ወድጃለሁ፤ ከሁሉ አስቀድሜ ግን የኳታር 
ስፖርት ኮሚቴ አባላት በቆይታችን ላሳዩን መልካምና 
ልባዊ መስተንግዶ በእናንተ በአንባቢዎቼ ስም ከፍ 
ያለ ምስጋናዬን እንዳደርስ ይፈቀድልኝ ዘንድ በትህትና 
እጠይቃለሁ፤ መልካም የንባብ ቆይታ፡፡

- ማሰታውቂያ -

Picture source-sc.qa

ኳታር 2022 የአለምዋንጫዝግጅት…
ታላላቆቹ አሜሪካንና አውስትራሊያን በማሸነፍ 
የ2022ቱን የፊፋ የአለም ዋንጫ አስተናጋጅነት 
ክብርን ካገኘች በኋላ በተለይም በምእራባውያን 
ሚዲያዎች ዘንድ የማስተናገድ እድሉን ያገኘችበት 
መንገድ ፍትሀዊ አይደለም ከሚል ጀምሮ፣ በሀገሪቱ 
ያለው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ለተወዳዳሪዎች ጤና 
አመች አይደለም እንዲሁም ስታዲየሞቹን እየገነቡ 
ያሉ የሶስተኛው አለም ዜጎች አያያዝና እንክብካቤ 
መሰረታዊ የሰው ልጅ መብትን ያላከበረነው የሚሉ 
ያልተቋረጡ ትችቶችን እያስተናገደች የምትገኘው 
ኳታር 22ኛውን የአለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ 
ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅ ክልል ለማስተናገድገና 
የአምስት አመታት እድሜ ቢቀራትም ስታዲየሞቹ 
መጠናቀቅ ካለባቸው 2020 ዓ.ም አስቀድማ ለማድረስ 
በትክክለኛው መንገድ እየተጓዘች እንደሆነ አዘጋጆቹ 
ገልጸውልናል፡፡ 
በምእራባውያን ሚዲያዎች ዘንድ ደጋግመን 
የሰማነውን የስታዲየም ግንባታ ሰራተኞች ኢ ሰብአዊ 
አያያዝን በተመለከተ በዚህ ጽሁፍ እንዳላጋራችሁ 
በቆይታችን ከነዚህ ሰራተኞች ጋር የመገናኘት 
እድል ፈጽሞ አላገኘንም፡፡ነገር ግን አዘጋጆቹ ከዚህ 
ቀደም የእግር ኳስ አፍቃሪው ህብረተሰብ አይቶት 
የማያውቀውን የአለም ዋንጫ እናስመለክታችኋላን 
ጠብቁን ሲሉ ይደመጣሉ፡፡
ለመሆኑ የኳታሩ የአለም ዋንጫን ከዚህ 
ቀደም ከነበሩ አለም ዋንጫዎች ለየት የሚያደርጉት 
ነገሮች ምንድንናቸው? እነሆ ምላሹን፡-
– ውድድሩ የሚካሄድባቸው ቦታዎች በቅርብ 
ርቀት መገኘት፡-

– የ2022 ዓ.ም የአለም ዋንጫን ለማስተናገድ 
ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት ከሚገነቡት 
ስምንት ዘመናዊ ስታዲየሞች እና የቡድኖቹ ማረፊያ 
ካምፖች እንዲሁም የደጋፊዎች መሳባሰቢያ ዞኖች 
እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በቅርብ ርቀት ውስጥ 
መገንባታቸው፣ ተጫዋቾቹ ከልምምድ ወደ ሆቴላቸው 
እና ስቴዲየም የሚያደርጉት ረዥም ጉዞን ማስቀረት 
በመቻሉ ለአላስፈላጊ ድካም እንዳይጋለጡ ከማድረጉ 
በተጨማሪ ደጋፊዎች ከአንዱ ስታዲየም ወደ ሌላኛው 
ስታዲየም ለመጓዝ የሚወስድባቸው ከፍተኛው 
የጊዜ ርቀት 1፡00 ሰአት ብቻ በመሆኑ በአንድ ቀን 
በስቴዲየም ተገኝቶ ሁለት እና ከዛ በላይ የአለም ዋንጫ 
ጨዋታዎችን የመከታተል እድልየሚፈጥርመሆኑ፡፡
– በስታዲየሞቹ ግንባታ ወቅት ቴክኖሎጂ ያለው ትልቅ ቦታ:-

Picture source-sc.qa 

ውድድሩን ካታር እንድታዘጋጅ 

ከተመረጠች ጀምሮ ከሚነሱ ወቀሳዎች አንዱ የቦታው 
ሞቃታማነት ነው፤ሀገሪቷም ለዚህ ቅሬታ ሁለት 
ምላሾችን አዘጋጅታለች እነሱም፣ የመጀመሪያው 
ውድድሩ በተለመዶ ከሚዘጋጅበት ሰኔ እና ሀምሌ 
ወሮች በአካባቢው በአመዛኙ ቀዝቃዛ ወቅቶች 
ወደሆኑት ህዳር እና ታህሳስ ማዛወር ሲሆን፣ 
ሁለተኛው ደግሞ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ 
ለተመልካቾች በየወንበሮቻቸው ስር የአየር ማቀዝቀዣ 
በመግጠም ለተጫዋቾች ደግሞ በስታዲየሙ ጣራ 
በኩል ቀዝቃዛ አየር እንዲገባ በማድረግ ለተጫዋቾች 
እና ለተመልካቾች ምቹ የአየር ሁኔታን መፍጠር 
ናቸው፤ ይህንን እኔም በአንዱ የሀገሪቱ ጨዋታ ላይ 
በአካል በመገኘት ለማረጋገጥ ችያለሁ፣ የስታዲየሙ 
የውጭውና የውስጡ የሙቀት ሁኔታ ፈጽሞ 
የተለያየነው፡፡
– ሀገሪቱ በመሰረተ ልማት ረገድ ያላት 
ዝግጁነት፡-
– እጅግ ዘመናዊ የአየር መንገድ፣ ሰፋፊ 
የየብስ መንገዶች፣ አለም ዋንጫውን ታሳቢ 
አድርጎ እየተገነባ ያለ የከተማ ውስጥ የባቡር 
መስመር፣ በርካታ ባለ ኮከብ ሆቴሎችና የእንግዳ 
ማረፊያዎች ከባህላዊ የበረሀ ላይ የድንኳን 
ማረፊያዎች ጋር ኳታር 2022 የአለም ዋንጫን 
ብለው ለሚመጡ እንግዶች ሁሉንም መሰረተ 
ልማቶች ከወዲሁ ያሟላች ሀገር በመሆኗ፡፡
– ኳታር ከአለም ዋንጫው በኋላ ትታው 
ለማለፍ ያሰበቸው አሻራ፡-
ይህንን የአለም 
ዋንጫ ለየት ከሚያደርጉት በርካታ ነገሮች 
አንዱና የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ይህ ሀገሪቱ 
ከውድደሩ በኋላ ትታው ማለፍ ስለምትፈልገው 
አሻራ እየሰራች ያለችው ስራ ነው፡፡ ይህም ማለት 
ኳታር ለውድድሩ ከሚገነቡ ስታዲሞች በአመዛኙ 
ስታዲየሙ በሚገነባበት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች 
ከውድድሩ በኋላ ከስፖርቱ እንዳይርቁና በመሰረተ 
ልማቶቹ በዘላቂነት እንዲጠቀሙባቸው ለማድረግ 
እየሰራች ያለችው ስራ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ 
ከስታዲየሞቹ የተወሰኑት ክፍሎች እየተገነቡ 
ያሉት በተገጣጣሚና ተነቃቃይ የስታዲየም 
ጣራዎች፣ የመቀመ ጫወንበሮችና ኮንክሪቶች 
ሲሆን ይህም ከውድድሩ መካሄድ በኋላ ለታዳጊ 
ሀገሮች እነዚህን የስታዲየም ክፍሎች በእርዳታ 
መልክ ለመስጠት ስላቀደች በመሆኑነው፡፡
– የአለም ዋንጫ በኳታር በመከናወኑ 
ኢትዮጵያውያን ምን እንጠቀማለን፡- ሀገራችን 
በውድድሩየመሳተፍ እድልን ብታገኝም ባታገኝም 
የኳታር የአለም ዋንጫ ከመቸውም ጊዜ በላይ 
ከሀገራችን በቅርብ ርቀት የሚከናወን የአለም 
ዋንጫ ይሆናል፡፡ በ2400 ኪ.ሜ ርቀት ላይ 
የምትገኘውን ኳታር በ4፡30 የአየር በረራ ብቻ 
በቀጥታ የውድድሩ ታዳሚ መሆን የምንችል 
ከመሆኑም በላይ በተመሳሳይ የሰአት አቆጣጠር 
ላይ መገኘታችን ደግሞ ጨዋታወቹን በየቤታችን 
በምቾት ለመከታተል የሚጠቅመንይሆናል፡፡
ከላይ በመጠኑ የጠቃቀስኳቸውንና ሌሎች 
በርካታ አስገራሚ ነገሮችን የያዘው የ2022 
የኳታር የአለም ዋንጫ እስካሁን ካየናቸው 
የአለም ዋንጫዎች የተለየውን የአለም ዋንጫ 
ሊያስመለክተን የአምስት አመታት እድሜ ብቻ 
ይቀረዋል፤ አዘጋጆቹየተለየውንጠብቁብለውናል፣ 
እውነት ይህ የአለም ዋንጫ የምንጊዜም ምርጡ 
የአለም ዋንጫ ይሆን? የዛሰውይበለን፡፡ 
ኳታር እና አጠቃላይ የስፖርት 
ውድድሮች መስተንግዶዋ
በመካከለኛው ምስራቅ የአለማችን ክፍል 
የምትገኘው ኳታር በ11,000KM² የቆዳ ስፋት 
እና 2.5 ሚሊየን የህዝብ ብዛት(ከነዚህም መካከል 
300,000 ብቻ ናቸው የኳታር ዜግነት ያላቸው 
የተቀሩት ደግሞ ስደተኞች ናቸው) ሚጢጢ 
የምትባል ነገር ግን ባላት የተፈጥሮ ነዳጅ ሀብት 
ምርት በመጠቀም በአለማችን ቀዳሚዋ ከፍተኛ 
የነፍስ ወከፍ ገቢ ባለቤት ዜጎች ሀገርም ነች፡፡
ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ከባህላዊው 
የግመል ውድድር አንስቶ የፈረስ፣ ቼዝ፣የሜዳ 
ቴኒስ፣የጎልፍ፣ አትሌቲክስ፣ የመኪና 
አሽቅድምድም እና ሌሎች በርካታ የስፖርት 
አይነቶችን ሳትለይ በቋሚነት በየሳምንቱ ቢያንስ 
አንድ አለም አቀፋዊ የስፖርት ውድድርን 
እያስተናገደች ትገኛለች፣ የ2019 የአለም 
አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የኳታር 2022 የአለም 
ዋንጫ አስተናጋጅም እንደሆነች ልብ ይበሉ፣ 
በዚህም ቀስ በቀስ የስፖርት ቱሪዝም ገቢዋን 
እያሳደገች እና በአለም አቀፉ መድረክም ከዋነኞቹ 
የስፖርቱ አለም ተዋናዮች አንዷ እየሆነች 
መምጣቷን ብዙዎች ይስማማሉ፡፡
ኳታር ለምን ስፖርቱ ላይ ይህን 
ያክል አተኮረች?

Picture source-sc.qa

የባርሴሎና ክለብ የማልያ ላይ ስፖንሰር 
፣ የፓሪስ ሴንት ዤርሜይን ክለብ ባለቤቶች፣ 
የግዙፉ አለም አቀፍ የስፖርት ኔትዎርክ ቢ 
ኢን ስፖርትስ መገኛ፣ ዲያጎማራዶና፣ ራውል 
ጎንዛሌዝ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ፣ ሰይዱ ኬታና 
ሌሎችም የእግር ኳስ ኮከቦች የእግር ኳስ 
ዘመናቸው ማብቂያ የማሰልጠኛና መጫዎቻ 
ክለቦች መገኛ፣ የግዙፎቹ አስፓየር የስፖርት 
አካዳሚ እና አፒ ስታር የስፖርት ህክምና 
ማእከል እንዲሁም ሌሎች በርካታ አስገራሚ 
የስፖርት መሰረተ ልማቶች መገኛ ነች፣ 
ጥያቄው ግን ይሄ ሁሉ ኢንቨስትመንት 
ለምን?ነው::
ለዚህ ጥያቄ ከተለያዩ አስተያየት 
ሰጭዎች እነዚህ ሶስት ምላሾች ተደጋግመው 
ይደመጣሉ፡ የመጀመሪያው ዜጎቿን 
ጤናማና ንቁ ለማድረግ እንደሆነና 
ወደ ስፖርቱ እንዲሳቡ፣የአካል 
ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያዘወትሩ 
ለማድረግ ሲሆን፤ ሁለተኛው 
አላማ ደግሞ ኳታርን ለመላው 
አለም ማስተዋወቅ ነው፣ በሁሉም 
አቅጣጫ ትኩረት በሚሰጠው 
የስፖርት ዘርፍ በመሳተፍ፣ 
በማዘጋጀትና ስፖንሰር በማድረግ 
የኳታርን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና 
ባህላዊ እሴቶችን ማስተዋወቅ ነው፡
፡ ሶስተኛውና ዋነኛው የኳታር 
የስፖርት ኢንቨስትመንት ትልቅ ግብ ግን 
ሄኛው ነው፡ እሱም ሀገሪቱ “ራዕይ 2030”
ብላ በሰየመችውና ከተፈጥሮ ሀብት ጥገኝነት 
የተላቀቀ ዘላቂ ኢኮኖሚን ለመገንባት 
በምታደርገው ርብርቦሽ ስፖርት አንዱ 
የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ ነው፡፡በዚህም 
መሰረት ኳታር በዘላቂነት የተለያዩ የስፖርት 
ውድድሮችን በማስተናገድና በተለያየ መንገድ 
በመሳተፍ የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል በመሆን 
ከነዳጅ በኋላ ባሉት ዓመታት ኢኮኖሚዋን 
እንዲደግፍላት ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች 
መሆኑ ነው፡፡
————– አበቃሁ —————

You Might Also Like

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

በሀገር ውስጥ ዘገባችን አዲስ አበባ ከተማን ለፕሪሚየር ሊጉ ያበቃው አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር እንግዳችን ነው….

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነቱን አረጋገጠ
Next Article የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ 24ኛ ሳምንት የጨዋታ ውጤት

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
U-20 ብሄራዊ ቡድንየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንሴካፋ

ከ 20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ መርሀ ግብር ይፋ ሆኗል !

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 5 years ago
የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ ውጤት /LIVESCORE/ ይከታተሉ
ጅማ አባጅፋር አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል!!
የጨዋታ ዘገባ| በቀጣይ አመት የትግራይ ክልል ከለቦች የማይሳተፋ ከሆነ በሊጉ የሚሳተፈዉ አንዱ ክለብ አዳማ ከተማ መሆኑ ታዉቋል!
ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ዝውውርን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?