መነሻ ገጽ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የክለቦች ዝግጅት | ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርስቲ
ቅድመ ውድድር ዝግጅትወልዋሎዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርስቲ

አጋራ
አጋራ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርስቲ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ማለትም ከ2016 የውድድር ዘመን ጀምሮ ዳግም መሳተፍ ከቻሉ የትግራይ ክልል ክለቦች መካከል አንዱ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ቢሆንም በሊጉ ውጤታማ በመሆን ረገድ ግን በእጅጉ ለተከታታይ አመታት ሲቸገር አስተውለናል። በተጠናቀቀው የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ካደረጋቸው 38 ጨዋታዎች 10 በማሸነፍ 16 አቻ በመውጣት 12 በመሸነፍ 32 ጎልን በማስቆጠር 36 ጎሎችን አስተናግዶ ክለቡ በ4 የጎል ዕዳ በመጨረሻው ሳምንታት በማስመዘገባቸው ውጤቶች እንዲሁም የሌሎች ክለቦችን ነጥብ መጣል ተከትሎ 46 ነጥቦችን በመሰብሰብ 16ኛ ደረጃን በመያዝ በሊጉ ለከርሞ መቆየቱን ማረጋገጥ መቻሉ ይታወሳል።

በሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ከውስጥ ችግሮቹ ጋር እየታገለ ላለመውረድ ትልቅ ውስጥ ክለቡ ቢገኝም በኢትዮጵያ ዋንጫ ግን ሲዳማ ቡናን በፍፃሜ መርሀግብር በመርታት በደስታ ጮቤ አመቱን በድል ማጠናቀቁን አረጋገጠ። የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ኢትዮጵያን በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመወከል የበቃው ክለቡ አስቀድሞ ለአህጉራዊ ውድድር እና ለ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋና አሰልጣኝ ግርማ ታደሠን ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ካሳካ በኋላ በመጨረሻም ወደ ዝውውሩ በመግባት አዳዲስ እና በክለቡ የነበሩ ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙን ጀመረ።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከሱዳኑ ሂላል አልሳህል ጋር ከተደለደለ በኋላ ከቡድኑ ባጣናቸው ተጫዋቾች ማለትም ፍሬው ሰለሞን (ጣቁሩ) ፣ ዩጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ ጆኤል ሙታክብዋን ፣ የመስመር አጥቂው ዳዊት ገብሩ ፣ ኪሩቤል ወንድሙ እና ኮንኮኒ ሀፊዝ እና ሌሎች ተጫዋቾች ምትክ በዝውውር መስኮቱ አጥቂው ካርሎስ ዳምጠውን ከወላይታ ድቻ ፣ ተከላካዩ በረከት ሳሙኤልን ከሀዋሳ ከተማ ፣ ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤልን ከኢትዮጵያ መድን ፣ ተከላካዩ አህመድ ረሺድ (ሺሪላ) ከድሬዳዋ ከተማ ፣ አማካዩ አቤል እንዳለን ከምድረገነት ሽረ ፣ አማካዩ በፍቃዱ አስረሳኸኝ (ፓግባ) ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ለሁለት ክለቦች ፈርሞ በመጨረሻም ማረጋገጫውን በማግኘት ለክለቡ የፈረመውን የመስመር አጥቂው እዮብ አለማየሁን ከሀድያ ሆሳዕና እና ተከላካዩ ዘረሰናይ ብርሀነን ከመቐለ 70 እንደርታ ቡድኑን መቀላቀል የቻሉ የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ሲሆን የውጪ ዜግነት ያላቸውን በ2018 አጋማሽ ላይ አርባምንጭ ከተማን የተቀላቀሉት አብዱራህማን መሐመድ እና ሴኔጋላዊው አማካይ ማማዱ ሴክን ፣ ጋናዊውን አማካይ ነስቲህ ኦሴን ከባህርዳር ከተማ ፣ ሴኔጋላዊውን ግብ ጠባቂ አማር ፎልን ከፒኪን እና ጋናዊውን አማካይ መሐመድ አብዱልባሲጥን ከጅቡቲው ቴሌኮም ክለብ በድምሩ ለወልዋሎ ፊርማቸውን ያኖሩ 12 አዳዲሶቹ የቡድኑ ፈራሚ ተጫዋቾች ናቸው።

ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ እንደ አፈወርቅ ሐይሉ ፣ ሠመረ ሀፍታይ ፣ በየነ ባንጃው ፣ ናሆም ሀይማርያም ፣ ነፃነት ገብረመድህን ፣ ሰምኦን ማሩ እና ናትናኤል ኪዳኔ ፣ ኪም ላም እና ሌሎች ሦስት ተጫዋቾች ጨምሮ በድምሩ በድምሩ ወደ 12 የሚደርሱ ነባር ተጫዋቾች ውላቸው ሲራዘም 5 ወጣት ተጫዋቾች ደግሞ ወደ ዋናው ቡድን ማደግ ችለዋል።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከሱዳኑ ሂላል አልሳህል ጋር መደልደላቸውን ተከትሎ ከነሀሴ 13/2018 ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዲስ አበባ ከተሰባሰቡ በኋላ በአዳማ ከተማ ዝግጅታቸውን የቀጠሉት ወልዋሎዎች በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ እና ረዳቶቻቸው እየተመሩ በቀን ሁለቴ እና አንድ ጊዜ ልምምዳቸውን አጠናክረው በመቀጠል ለአህጉራዊ ውድድራቸው ይረዳቸው ዘንድ የወዳጅነት ጨዋታን ማድረግ የቻሉ ሲሆን ከመቻል ጋር 2ለ2 በባህርዳር ከተማ ከተማ ደግሞ 1ለ0 ከተሸነፉ በኋላ ከሱዳኑ ሂላል አልሳህል ጋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጪ 2ለ1 ሽንፈት ቢያስተናግዱም በድሬዳዋ ስታዲየም ግን በካርሎስ ዳምጠው ድንቅ ብቃት በመታገዝ 2ለ1 በማሸነፍ በመጨረሻም በተሰጠው የመለያ ምች የ5ለ4 ድምር ውጤት በማስመስገብ በሁለተኛው ዙር ከሊቢያው አልሀሊ ትሪፓሊ ጋር የሚገናኙ ሲሆን ጥቅምት 6/2019 በድሬዳዋ ስታዲየም ከሚደረገው ጨዋታ በፊት ግን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታውን ወልዋሎ ወደ ቁሊቶ በማምራት ሀላባ ከተማን ዕርብ መስከረም 29/2019 የሚያደርግ ሲሆን ከዚህ ጨዋታ በፊት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የመጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታውን አድርጎ 3ለ1 በመሸነፍ ወደ ሊጉ ውድድር እንደሚያመራም ሀትሪክ ስፖርት በመረጃው መገንዘብ ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...