መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ቡና ከፍተኛ ገንዘብ ያስገኘለትን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ፈፀመ
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ከፍተኛ ገንዘብ ያስገኘለትን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ፈፀመ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ከረጅም ጊዜ አጋሩ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ ጋር አዲስ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ውል ተፈራረመ።

ፋብሪካው ባለፉት ሶስት ዓመታት በየዓመቱ 22.5 ሚሊዮን ብር ለክለቡ ሲከፍል ቆይቷል። በአዲሱ ስምምነታቸው መሰረት ግን ሐበሻ ቢራ በስፖንሰርሺፕ ብቻ ዓመታዊ 45 ሚሊዮን ብር ይከፍላል።

ከዚህ ዋናው የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በተጨማሪ ከእያንዳንዱ የሐበሻ ቢራ የጠርሙስ እና የድራፍት ሽያጭ ላይ ፋብሪካው በዓመት ከ13-15 ሚሊዮን ብር ለክለቡ የሚያበረክት ይሆናል። በድምሩ ኢትዮጵያ ቡና በዚህ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ከ174-180 ሚሊዮን ብር ያገኛል ማለት ነው። ይህም በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ከአንድ ካምፓኒ ጋር የተደረገ ከፍተኛ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በመሆን በሪከርድነት ሊመዘገብ ችሏል።

ይህም ብቻ ሳይሆን ክለቡ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ሐበሻ ቢራ ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ የሚያበረክት ይመስላል።

ይሄንን ተከትሎ “ይህ የሽልማት ገንዘብ ለአንዴ ብቻ ነው ወይ?” የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የክለቡ ምክትል የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ይስማሸዋ ስዩም “ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ቡና ሻምፒዮን ለመሆን ይብቃ እንጂ ሶስቱን ዓመታት ሻምፒዮን ከሆነም በድምሩ 45 ሚሊየን ብር በሽልማት መልክ እናገኛለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...