መነሻ ገጽ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የክለቦች ዝግጅት | ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ቅድመ ውድድር ዝግጅትኢትዮ-ኤሌክትሪክዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ኢትዮ ኤሌክትሪክ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግን ከመሠረቱ ክለቦች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱ ምን ይመስላል።

የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግን ከመሠረቱ ክለቦች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ስመ ጥሩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሊጉ በሁለት አጋጣሚዎች መውረዱ የሚታወስ ሲሆን በ2017 የውድድር ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ከተመለሰ በኋላ ግን ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት እየተካፈለ ይገኛል። በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ ባሳለፉነው የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተሻለውን ደረጃ ይዞ መቋጨት የቻለው ክለቡ 38 የሊግ ጨዋታዎች በማድረግ 13 አሸንፎ 15 የአቻ ውጤቶች 10 ሽንፈቶችን በማስተናገድ 32 ጎሎችን በተጋጣሚው መረብ በማስቀመጥ በተቃራኒው 26 ጎሎችን አስተናግዶ በ6 ንፁህ የግብ ክፍያ 54 ነጥቦችን ሸምቶ 5ተኛ ደረጃን በመያዝ አመቱን ለማጠናቀቅ መብቃቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

ከወራቶች በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ ከመካፈሉ ቀደም በማለት ሁለት አመታትን ቡድኑን ሲያሰለጥኑ የነበሩትን የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ውል አራዝሞ በሦስተኛ የውድድር ዘመናቸው አሰልጣኙ ካለፈው በተሻለ ማድረግ እንዲችሉ ዳግም ሀላፊነትን በመስጠት በመቀጠል ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ሀገር በድምሩ አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ዝውውሩ ገብቶ በማስፈረም የአስር ነባሮችን ውል ደግሞ ማራዘም ችሏል። አዳዲስ ክለቡን የቀላቀሉት ባለ ልምድ እና ወጣት ተጫዋቾችን ስንመለከት ተከላካዩ አስቻለው ታመነን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ አማካዩ ናትናኤል ዘለቀን ከሸገር ከተማ ፣ የግራ መስመር ተከላካዩ ፍራኦል መንግስቱን ከሲዳማ ቡና ፣ ተከላካዩ አቤል አየለን ከሸገር ከተማ ፣ አማካዩ እንዳልካቸው መስፍን የግራ መስመር አጥቂው አሸናፊ ተገኝ እና የመሐል ተከላካዩ አካሉ አትሞን ሦስቱንም ከአርባምንጭ ከተማ ፣ የመስመር አጥቂው አንዋር ሙራድን በድጋሚ ከፋሲል ከነማ የመለሰ ሲሆን ከከፍተኛ ሊጉ ደሴ ከተማ የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አማኑኤል ግዛቸው እና የመስመር አጥቂው እሱባለው ሙሉጌታን ከአንደኛ ሊጉ ዱራሜ ከተማ ደግሞ ተከላካዩ አንዱአለም ስዩምን ወደ ስብስቡ በአዲስ መልክ ሲያካትት በመቻል ቆይታ የነበረውን ዩጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ አሊዮንዚ ናፊያን እና የጋቦን ፕሪምየር ሊግ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ጋቦናዊውን አጥቂ ካሌብ ንዛምባን ከሀገሩ ክለብ ቫውቱር ደ ሊብሬቪል በይፋ ማስፈረሙን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።

ክለቡ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ ወሳኙን አጥቂው አቤል ሀብታሙን ጨምሮ ሀብታሙ ሸዋለም ፣ አንዋር በድሩ ፣ ሔኖክ ገብረህይወት ፣ አሸናፊ ጥሩነህ ፣ ሙከረም ረሺድ ፣ ኪሩቤል ሐይሉ ፣ አብዱልመጅድ ሁሴን ፣ ናትናኤል ዱባለ እና አብነት ተስፋዬን ውላቸው ያራዘመላቸው አስሩ ነባር ተጫዋቾች ሲሆኑ አሸናፊ መላኩ ፣ ብሩክ ዘላለም እና ብሩክ ታምራት ደግሞ ወደ ከ20 አመት በታች ቡድን ወደ ዋናው ማደግ የቻሉ ተጫዋቾች ሆነዋል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እና ረዳቶቻቸው እየተመሩ ለ2019 የውድድር ዘመን ከነሀሴ 20/2018 ጀምሮ ከአዲስ አበባ የጀመሩትን የዝግጅት ምዕራፍ ወደ አዳማ ከተማ በመቀየር በከተማው ከቀን ሁለቴ እስከ አንድ ጊዜ ድረስ በጂም እና በሜዳ ተግባራት ራሳቸውን ሲያዘጋጁ የከረሙ ሲሆን ቅድመ ዝግጅታቸው ምን እንደሚመስል ለመለካት ደግሞ አራት የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ የገመገሙ ሲሆን በመቻል የ2ለ0 በባህርዳር ከተማ 3ለ2 ሲሸነፉ ኢትዮጵያ መድንን 2ለ0 በወንጂ ከተማ ከሚገኙ የስብስብ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ደግሞ 4ለ0 በማሸነፍ የቅድመ ውድድር ጨዋታቸውን አገባደዋል። የ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቀጣዩ ሳምንት ዕርብ መስከረም 29 ሲጀመር በሜዳቸው አዲስ አበባ ስታዲየም አዳማ ከተማን በማስተናገድ የውድድር ዘመናቸውን በይፋ ይጀምራሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...