መነሻ ገጽ ዜናዎች 2ኛ ዙር የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለመጨረስ ግንባታው እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ
ዜናዎች

2ኛ ዙር የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለመጨረስ ግንባታው እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ

አጋራ
አጋራ

የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን የ2ኛ ዙር የብሔራዊ ስታዲየም ግንበታ ሂደትን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላ ለተለያዩ ሚዲያ ተቋማት ማብራሪያ ሰጠዋል ፡፡

በገለፃው የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር የስፖርት ልማት ሪፎርምን መነሻ በማድረግ ስፖርቱ በህግና ስርዓት እንዲመራ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን፣የስልጠና ማዕከል እና የማዘወተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ትኩረት ያገኙበት ሁኔታ መኖሩን፣
በአገራችን ለአገር ውስጥም ሆነ ኢንተርናሽናል ስታንደርድ ያሟሉ አማራጭ ሜዳዎች እንዲኖሩ የተጀመሩ ስታዲየሞች
ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ ጥረት እየተደረገ ያለበት ሁኔታ መኖሩን እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን
በስፋት አስረድተዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም የ2ኛ ዙር ብሔራዊ ስታዲየም በግብአት አቅርቦት፣በሰው ኃይል እጥረት እና በኮቪድ-19 መከሰት ምክንያት የግንባታው ሂደት የተስተጓጎለበት ሁኔታ ቢኖርም፤ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለመጨረስ በመንግስት ጭምር ትኩረት ተሰጥቶት መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ከዋናው ስታዲየሙ ውጪ በዙሪያው እየተገነቡ ያሉትን የስታዲየሙ ጣራ ተሸካሚ ኮለኖችን፣የስብሰባ አደራሾች እና የመለማመጃ ሜዳዎች
የሚገነቡበትን ስፍራዎችንና ሌሎች መሰል ግንባታዎችን ተዟዙረው ተመልክተዋል፡፡

© federal sport commission

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...