አብዲሳ ጀማል የቀድሞው ክለቡን ኢትዮጵያ መድህንን ተቀላቀለ።

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች ወደ አርባምንጭ ተጉዘው አዲስ አዳጊውን ክለብ ጋሞ ጨንቻን የሚገጥሙ ሲሆን ቡድናቸውን ማጠናከራቸውን ቀጥለው አጥቂው አብዲሳ ጀማልን አስፈርመዋል።
የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ፣ አዳማ ከተማ እና እንዲሁም ከኢትዮጵያ መድን ቆይታው በኋላ የተጠናቀቀውን አመት በድሬዳዋ ያሳለፈው ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ውል ቢኖረውም በጠየቀው የልቀቁኝ ጥያቄ መሠረት ከክለቡ ጋር በመለያየት ማረፊያው የቀደመ ክለቡ ኢትዮጵያ መድን ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ