በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ላለፉት አመታት ከተመለከትናቸው ጥሩ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን የቻለው እንዳለ ዮሐንስ አዲስ የኢትዮጵያ መድን ተጫዋች ሆኗል።

ከኢንጅነሪንግ ሙያው ጎን ለጎን በእግር ኳሱ ከሀምበሪቾ ዱራሜ የተነሳው እና በክለቡ በነበረው ቆይታም ጥሩ ጊዜን በማሳለፉ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቶ ላለፉት ሦስት አመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ በሀምበሪቾ ካሰለጠኑት አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ጋር በድጋሚ መገናኘቱ ዕርግጥ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ