መቻል የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን አስፈረመ
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት መቻሎች ሁለት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል። በቅርቡ ለሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የደረሰው የተከላካይ አማካዩ ሙዳቲር ያህያ መሐመድ እና የላይቬሪያ ዜግነት ያለው አማካዩ ሞሪስ ኬኔህ ሁለቱም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ካሰለጠኑት የደቡብ ሱዳኑ ክለብ ጃሙስ በአንድ አመት ውል በቀጥታ ፊርማ እና በውሰት ውል አስፈርመዋል።
አስተያየት ይስጡ