ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደጉት ጋሞ ጨንቻዎች የፊታችን ዕርብ ዝግጅቱን የሚጀምር ይሆናል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደጉት ጋሞ ጨንቻዎች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካፈሉበት የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዝግጅት የሚጀምሩበትን ቀን ክለቡ በላከልኝ መረጃ አሳውቆኛል። በአሳዳጊ አሰልጣኛቸው ማቲዮስ ለማ የሚመራው ክለቡ 19 የቦርድ አባላትን አዋቅሮ ወደ ዝውውሩ ከገባ በኋላ አጥቂው መሐመድ ናስርን ከቤንች ማጂ ፣ ሳሙኤል ጃጊሶን ከባቱ ከተማ እንዲሁም ደግሞ አማካዩ አቤኔዘር ህዝቄልን ከሸገር ከተማ ማስፈረም የቻለ ሲሆን የስምንት ነባር ተጫዋቾችን ውልም አራዝሟል።
በቀጣዩ ቀናት አራት የውጪ ዜጋን ጨምሮ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርም የሚጠበቀው ክለቡ ከፊታችን ዕርብ ነሀሴ 15/2018 ጀምሮ በአርባምንጭ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚጀምር ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ