መነሻ ገጽ አዳማ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
አዳማ ከተማወልቂጤ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

አጋራ
አጋራ

በዋና ዳኛ ሀይለየሱስ ባዘዘው የተመራዉ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ በ10:00 ሲል በተጀመረው። ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ በተወሰኑ የእግርኳሱ ቤተሰቦች ታጅቦ የተካሄደዉ ጨዋታም ማራኪ የሚባል ጨዋታን አስመልክቶናል።

በቀልቂጤ ከተማ በኩል በ 4 3 3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት አሰልጣኝ ጳዉሎስ ጌታቸዉ ይበልጥ መሀል ክፍሉ ላይ የበላይነት ነበራቸዉ። አማካዮቹ ፍሬዉ ሰለሞን እና አአብዱልከሪም ወርቁ የነበራቸዉ ጥምረትም ፍሬያማ ነበር ማለት ይቻላል በለተይ ለመስር አጥቂዉ አቡበከር ሳኒ ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ኳሶችን ሲያደርሱም ተመልክተናል። በጨዋታዉም ረመዳን የሱፍ በመስመር በኩል ድንቅ እንቅሰቃሴ ማድረግም ተችሏል።

በአንፃሩ አዳማ ከተማዎች ሀይልን ቀላቅለዉ በመጫዎት ወደ ወልቂጤ የግብ ክልል በተደጋጋሚ ሲደርሱ ነበር በተለይ በአጥቂያቸዉ አብዲሳ ጀማል አማካኝነት ጥሩ ጥሩ ሙከራ ቢያደርጉም በአንጋፋው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰዉ አማካኝነት ግብ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል። ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ የሚባል ጨዋታን አስመልክተዉን ያለምንም ግብ የመጀመሪያውን አጋማሽ አጠናቀዉ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ከእረፍት መልስም የወልቂጤዉ የግራ መስመር ተጫዋች ረመዳን የሱፍ በ52ኛዉ ደቂቃ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት በአህመድ ሁሴን ተቀይሮ ለመዉጣት ተገዷል።

ጨዋታዉ ቀጥሎ 65ኛዉ ደቂቃ ላይ አብዲሳ ጀማል ከግብ ጠባቂዉ ጀማል ጋር ብቻዉን ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት የቀረዉ በአዳማ በኩል የሚያስቆጭ ሙከራ ነበር።

80ኛዉ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባዉ አህመድ ሁሴን ግብ ቢያስቆጥርም የእለቱ ዳኛ ከጨዋታ ዉጭ በማለት ሽረዉታል። የዳኛዉን ዉሳኔ ያልተቀበሉ ተጠባባቂ ተጫዋቾች እና የአስልጣኝ ክፍሎች ጠንከር ያለ ትችትን ሲሰነዝሩም ተስተዉሏል።

በጨዋታዉ መገባደጃ 88ኛዉ ደቂቃ ላይም ተቀይሮ የገባዉ ሄኖክ አየለ ከግብ ጠባቂዉ ጋር ብቻዉን ተገናኝቶ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በዚህ መሰረትም የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታዉም ያለ ምንም ግብ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል።

ደረጃ ሰንጠረዥና ቀጣይ መርሐግብር 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...