መነሻ ገጽ ሀምበሪቾ ድራሜ የጨዋታ ዘገባ | ጅማ አባጅፋር ወሳኝ ድል ቀንቶታል
ሀምበሪቾ ድራሜዜናዎችየጨዋታ ዘገባጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ዘገባ | ጅማ አባጅፋር ወሳኝ ድል ቀንቶታል

አጋራ
አጋራ

በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኙ የነበሩት ሁለቱ ክለቦች ጨዋታቸዉን በወጣላቸው መርሀግብር መሰረት እኩለ ቀን 7:00 ሲል በጀመረው ጨዋታ ተመጣጣኝ የሚባል የኳስ ፍሰት በተመለከትንበት የሁለቱ ቡድኖች  ጨዋታ በጅማ አባጅፋር በኩል ወደ መስመር ያተኮረ የአጨዋወት መንገድን ለመተግበር ሲሞክሩ የታዘብን ሲሆን በአንፃሩ ሀምበሪቾ ዱራሜዎች ደግሞ በመሀል ተጫዋቾቻቸዉ ፀጋአብ ዩሴፍ እና ሮቦት ሰለሞን ወደፊት ለመሄድ ጥረት ሲያደርጉ ተመልክተናል።

ጅማ አባጅፋሮች በተደጋጋሚ ረጃጅም ኳሶችን ወደ መስመር በመጣል ወደ ተጋጣሚ ቡድን የግብ ክልል ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት እንዳለ ሆኖ ለጥንቃቄ በሚመስል መልኩ ተከላካዮቹን ይበልጥ በመጠቅጠቅ የተቃራኒ ቡድንን የማጥቃት አቅም ሲያዳክሙ እና ሲያከሽፋም ተመልክተናል።

 

ተጋጣሚዉ ሀምበሪቾም አልፎ አልፎ ከሚያደርጓቸው ሙከራወች በዘለለ በደንብ ወደፊት ገፍተዉ በመጫዎት ጫና ለማድረግ በማሰብ በአንድ ሁለት ቅብብሎሽ ወደ ጅማ የግብ ክልል ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት ዉጤታማ አልነበረም።

ከእረፍት መልስ ገና ጨዋታዉ እንደተጀመረ በእለቱ ድንቅ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ አማካዩ ንጋቱ ገ/ስላሴ በ46′ ደቂቃ ግሩም ግብ አስቆጥሮ ጅማ አባጅፋርን መሪ ማድረግ ቻለ።

ከግቡ መቆጠር በኋላ ሁለቱ ቡድኖች በእንቅስቃሴ ረገድ ተቀዛቅዘዉ ጨዋታቸዉን በዚሁ ዉጤት አጠናቀዋል።

ደረጃ ሰንጠረዥና ቀጣይ መርሐግብር 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...