መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | የጌታነህ ከበደ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ወልቂጤ ከተማን ከሽንፈት ታድጓል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | የጌታነህ ከበደ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ወልቂጤ ከተማን ከሽንፈት ታድጓል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ የተገናኙት ወልቂጤ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 1 – 1 በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል ።

ወልቂጤ ከተማ በ19ኛው ሳምንት ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ በተሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 አራት ለውጦችን አድርገው የገቡ ሲሆን ሮበርት ኦዶንካራን ፤ ፋሲል አበባየሁን ፤ ዮናስ በርታን እና በሀይሉ ተሻገር በሰይድ ሀብታሙ ፤ አበባው ቡጣቆ ፤ አክሊሉ ዋለልኝ እና በሀብታሙ ሸዋለም ምትክ ሲያሰልፉ ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ በሳምንቱ ጅማ አባጅፋርን በረቱበት ጨዋታ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ለውጦችን በማድረግ ከድር ኸይረዲንን ፤ ብሩክ ቃልቦሬን እና ዳንኤል ሀይሉን በአማረ በቀለ ፤ አባይነህ ፌኖ እና አብዲራህማን ሙባረክ ምትክ ጨዋታውን እንዲጀምሩ አድርገዋል ።አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ የጀመረው ጨዋታ ገና በጊዜ ነበር ግብ ያስተናገደው ። እንየው ካሳሁን ከቀኝ መስመር ላይ ያሻገረውን ኳስ ሄኖክ አየለ በግንባር ገጭቶ በሮበርት ኦዶንካራ መረብ ላይ በማሳረፍ ድሬዳዋ ከተማን መሪ አድርጓል ። በ7ኛው ደቂቃ ላይም ድሬዳዋ ከተማዎች በእንየው ካሳሁን አማካኝነት ያደረጉት የግብ ሙከራ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ወጥቷል ።ወልቂጤ ከተማዎች ደቂቃዎች እየገፉ ሲሄዱ በኳስ ቁጥጥሩ የበላይነት በመውሰድ እና ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ ከድሬዳዋ ከተማ ተሽለው የታዩበት ነበር ። ምንም እንኳን የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ ቢቸገሩም በተወሰኑ አጋጣሚዎች ለግብ የቀረቡ ዕድሎችን መፍጠር ችለው ነበር ።

በ16ኛው ደቂቃ ላይ አብዱልከሪም ወርቁ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብ ክልል ያሻገረውን ኳስ በሀይሉ ተሻገር ሳይደርስበት ቀረ እንጂ ለወልቂጤ ከተማ ግብ ማግኘት የሚችሉበት ዕድል ነበር ።

በ30ኛው ደቂቃ ላይ የወልቂጤ ከተማዎች ጥሩ የኳስ ቅብብል ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሳጥን በጌታነህ አቀባይነት ለዮናስ በርታ ደርሶ የነበረ ቢሆንም የዮናስ ኳስ ኢላማውን የጠበቀ አልነበረም ።

ድሬዳዋ ከተማዎች የኋላ ክፍላቸውን በማጠናከር ግብ ሳያስተናግዱ ወደ ዕረፍት ለማምራት የተሳኩ ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በወልቂጤ ከተማ በኩል በአየር ወደ ግብ ክልል የሚያደርሷቸው ኳሶች በቀላሉ ይበላሹባቸው ነበር ። የመጀመሪያው አጋማሽም በድሬዳዋ ከተማ የ1 – 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።በሁለተኛው አጋማሽ ወልቂጤ ከተማዎች በማጥቃቱ ተጠናክረው የቀረቡበት እና የድሬዳዋ ከተማን የኋላ መስመር በተደጋጋሚ ለመፈተን ጥረቶችን ያደረጉበት ቢሆንም የድሬዳዋ ከተማ የተከላካይ መስመር በቀላሉ ዕጅ የሚሰጥ አልነበረም ።

በድሬዳዋ ከተማ በኩል አልፎ አልፎ የሚያደርጓቸው የመልሶ ማጥቃት ሙከራዎች በቀላሉ በወልቂጤ ከተማ ተጫዋቾች ይበላሹም ነበር ። አጋማሹ ፈጠን ያለ እንቅስቃሴ ሊያሳየን ቢችልም በግብ ሙከራዎች ረገድ ግን ደከም ያለ ነበር ።ጌታነህ ከበደ በ75ኛው ደቂቃ ላይ ከቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ የሞከረው እና በፍሬው ሰለሞን የተመለሰው ኳስ በሁለተኛው አጋማሽ የታየው የመጀመሪያው ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ነበር ።

ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ ጋዲሳ መብራቴ በሳጥን ውስጥ በረመዳን የሱፍ ላይ የሰራው ጥፋት ለተመስገን ዳና ተጫዋቾች የፍፁም ቅጣት ምት ያስገኘ ሲሆን የቡድኑ አምበል ጌታነህ ከበደ ኳስ እና መረብን በማገናኘት የጨዋታውን ውጤት ወደ 1 – 1 ቀይሮታል ።በመጨረሻውቹ ደቂቃዎች ላይ በተለይም ወልቂጤ ከተማዎች የማሸነፍያውን ግብ ለማግኘት ከተጋጣሚያቸው በተሸላ መንቀሳቀስ ቢችሉም በሁለቱም በኩል ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል ።

ውጤቱን ተከትሎ ወልቂጤ ከተማ ነጥቡን 25 ማድረስ ቢችልም በደረጃው ላይ ለውጥ ያላመጣ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ በኩል ግን ነጥቡን 20 በማድረስ ለጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ ከተማ ተነጥቆ የነበረውን 13ኛ ደረጃ መልሶ ተረክቧል ።በ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሚያዝያ 23 ( ዕሁድ ) ቀን 9 ሰዓት ላይ ወልቂጤ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ሲጫወት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ሰበታ ከተማን የሚገጥም ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...