መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ በሄኖክ አዱኛ ብቸኛ ግብ ከጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ ወስደዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ በሄኖክ አዱኛ ብቸኛ ግብ ከጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ ወስደዋል

አጋራ
አጋራ

በስምንተኛው ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ ቀዳሚ ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና በቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል ተደርጎ ሄኖክ አዱኛ ከርቀት መቶ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ፈርሰኞቹ ሙሉ ሶስት ነጥቦ ይዘው ወጥተዋል ።

ወላይታ ድቻዎች በሰባተኛው ሳምንት በባህርዳር ከተማ በተሸነፉበት ጨዋታ ከተጠቀሙት ቋሚ አስራ አንድ የሶስት ተጫዋቾች ቅያሪ በማድረግ ወንድወሰን አሸናፊ ፤ አንተነህ ጉግሳ ፤ ደጉ ደበበ እና እድሪስ ሰዒድን ቀይረው ሲያስገቡ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ከአዳማ ከተማ ጋር አቻ ከተለያየው ቡድን ከነአን ማርክነህን ብቻ በመቀየር ጨዋታውን ጀምረዋል ።

በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊሶች በኳስ ቁጥጥሩ የተሻለ በመሆን ጨዋታውን የጀመሩ ሲሆን በሙከራ ደረጃም የተሻለ እንቅስቃሴን ማድረግ ችለው ነበር ።

12ኛው ደቂቃ ላይ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከአቤል ያለው በሳጥን ውስጥ ሆኖ የደረሰውን ኳስ አረጋግቶ ወደ ግብ ቢሞክረውም በግብ ጠባቂው ተመልሶበታል ። ከአራት ደቂቃዎች በኋላ አቤል ያለው ከከንአን ማርክነህ የተቀበለውን ኳስ ይዞ በሳጥን ውስጥ በመግባት ያደረገው ሙከራ በግብ ጠባቂው በድጋሚ ተመልሶበታል ።

ጫና በማሳደር የቀጠሉት ፈረሰኞቹ በሀያ ሶስተኛ ደቂቃ ላይ ከነአን ማርክነህ ያገኘውን ጥሩ አጋጣሚ ወደ ግብ ሳይቀይረው መቅረቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር ። በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በወላይታ ድቻ ሜዳ ላይ አብዛኛው ጊዜ በማሳለፍ ግብ ለማኘት ያደረጉት ጥረት ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል ። የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የተወሰደባቸው የጦና ንቦቹ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በመልሶ ማጥቃት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን ቢያደርጉም የመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም በኩል ግብ ሳይቆጠርበት ተጠናቋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ በአብዛኛው በመጀመሪያው አጋማሽ የታየው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ወላይታ ድቻዎች አጥቂያቸውነሰ ስንታየሁ መንግስቱን ማጣታቸው በብዙ መልኩ ክፍተት እንደፈጠረባቸው በግልፅ ታይቷል ። ፈረሰኞቹ በአጋማሹ ያደረጉት የግብ ሙከራ 48ኛው ደቂቃ ላይ በእስማኤል ኦጎሮ አማካኝነት ሲሆን ከያብስራ የተሻገረለትን ኳስ ተቆጣጥሮ ወደ ግብ ቢሞክረውም በወላይታ ድቻ ተከላካይ ተመልሶ የማዕዘን ምት ሆኗል ።

በመልሶ ማጥቃት ዕድሎችን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ የነበሩት የጦና ንቦቹ 56ኛ ደቂቃ ላይ በእድሪስ ሰይድ እና በምንይሉ ወንድሙ ጥሩ ቅብብል ወደ ግብ ያደረጉት ሙከራ ለጥቂት ከግቡ አናት በላይ ወቷል ። ግብ ለማግኘት የወላይታ ድቻን የተከላካይ መስመር በተደጋጋሚ ሲያንኳኩ የነበሩት ፈረሰኞቹ 65ኛ ደቂቃ ላይ በሄኖክ አዱኛ ግሩም ግብ መሪ መሆን ቻሉ ። በአቤል ያለው ከማዕዘን የተሻገረለው ኳስ በወላይታ ድቻ ተከላካይ ሲመለስ ያገኘው የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ አክርሮ በመምታት አስቆጠረ ።

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ፈረሰኞቹ ያስቆጠሩትን ግብ አስጠብቀው ለመውጣት የተጫወቱበት ነበር ። የጦና ንቦቹ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ያደረጉት ጥረት በአጥቂ መስመራቸው ክፍተት ምክንያት ሳይሳካላቸው ቀርቷል ። በስተመጨረሻም ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።

ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 14 በማድረስ ብዙ ግብ ባስቆጠረ በሚለው 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በበከሉ በ13 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...