መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ ከተማ በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ሙሉ ሶስት ነጥብ አሳክቷል
ሰበታ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ ከተማ በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ሙሉ ሶስት ነጥብ አሳክቷል

አጋራ
አጋራ

በስምንተኛው ሳመንት የመጨረሻ ጨዋታ ሁለቱ በሊጉ ግርጌ የሚገኙትን አና አስካሁን ምነም ማሸነፍ ያልቻሉት ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር ተገናኝተው በንታምቢ ብቸኛ የግብ ሰበታ ከተማዎች አሸንፈው መውጣት ችለዋል ።

ጅማ አባጅፋር በሰባተኛው ሳምንት ጨዋታ ከአርባምንጭ ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሁለት ቅያሪ በማድረግ ሚኪያስን ግርማን እና እዮብ አለማየሁን ወደ ጨዋታው ሲያስገቡ በሰበታ ከተማ በኩል በሀዋሳ ከተማ ከተሸነፈው ቋሚ አሰላለፍ ስድስት ለውጦችን በማድረግ የገቡ ሲሆን ተጫዋቾቹም ለአለም ብርሀኑ ፤ ቢያድግልኝ ኤሊያስ ፤ ጌቱ ሀይለማርያም ፤ ፍፁማ ተፈሪ ፤ ክሪስቶዝም ንታምቢ እና ፍፁም ገብረማርያም ናቸው ።

ሁለቱም ክለቦች በዚህ የውድድር አመት ምንም ጨዋታ አለማሸነፋቸውን ተከትሎ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ የገቡበት ጨዋታ ሲሆን በተለይም ሰበታ ከተማዎች በማጥቃቱ ረገድ የተሻሉ ነበሩ ። በጨዋታው የመጀመሪያ ሙከራ የተደረገው በ13ኛው ደቂቃ ላይ ሲሆን ሀይለሚካኤል አደፍርስ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ፍፁም ገብረማርያም ወደ ግብ ሞክሮት በግብ ጠባቂው ተመልሶበታል ። ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ሳሙኤል ሳሊሶ በረጅም የተላከለትን ኳስ ወደ ግቦ ሞክሮት የነበረ ቢሆንም የግብ ዘቡ አላዛር ማርቆስ አድኖበታል ።

በጨዋታው 27ኛ ደቂቃ ላይ የስታድየሙ የተወሰኑ መብራቶች መጥፋታቸው ተከትሎ ጨዋታው ለ14 ያህል ደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር ። በቀጣዮቹ የመጀመሪያ አጋማሽ ደቂቃዎች የሰበታ ከተማዎቾ የበለጠ የበላይነት የታየበት ሲሆን በሜዳ ክፍላቸው በዛ ብለው በመከላአሉ ላይ የተወጠሩች ጅማ አባጅፋሮ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ካደረጓቸው ኢላማቸውን ካልጠበቁ ሙከራዎች ውጪ ያን ያህል ጫና መፍጠር ያልቻሉበት ነበር ።

በሁለተኛው አጋማሽ በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ በሚመስል መልኩ የማጥቃት ፍላጎቶች የታዩበት ነበር ። ምንም እንኳን ወደ ግብ ክልል ሲደርሱ የሚያደርጉት ጥረት ደካማ መሆን በቀላሉ የግብ ዕድሎችን ከመፍጠር ቢያግዳቸውም ።

80ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳሊሶ ያሻማውን የቅጣት ምት ክሪስቶዚም ንታምቢ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር ሰበታ ከተማን መሪ አደረገ ። በቀሩት ደቂቃዎች የአሸናፊ በቀለ ተጫዋቾች ቀደም ብሎ ከነበረው በተሻለ ያደረጉት የመጨረሻ ደቂቃዎች እንቅስቃሴ ስኬታማ ሳይሆን በሊጉ ከዘጠኝ ጨዋታ ስምንተኛ ሽንፈታቸውን ለማስተናገድ ተገደዋል ።

ውጤቱን ተከትሎም ሰበታ ከተማ ነጥቡን 7 ቢያደርስም ባለበት 15ኛ ደረጃ የቀጠለ ሲሆን ጅማ አባጅፋርም በተመሳሳይ መልኩ ባለበት 16ኛ ደረጃ ላይ ረግቷል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...