መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | የማማዱ ሲዲቤ የመጀመሪያ አጋማሽ ሀትሪክ ድሬዳዋ ከተማን አሸናፊ አድርጓል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ዘገባ | የማማዱ ሲዲቤ የመጀመሪያ አጋማሽ ሀትሪክ ድሬዳዋ ከተማን አሸናፊ አድርጓል

አጋራ
አጋራ

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በውድድር አመቱ ምንም ነጥብ ማግኘት ያልቻለውን ጅማ አባጅፋር ከ ድሬዳዋ ከተማ አገናኝቶ ድሬ ከተማ በማማዱ ሲዲቤ ሀትሪክ ጨዋታውን 3 ለ 1 አሸንፏል ።

ጨዋታው ከጅማሮው ፈጠን ያለ እንቅስቃሴን ያሳየ ነበር ። በተለይም ጅማ አባጅፋሮች ከቀኝ መስመር ላይ በሚሻገሩ ኳሶች ቀድመው ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን ቢያደርጉም በድሬደዋ ግብ ጠባቂ ተመልሶባቸዋል ። በተለይም 4ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻገረ ኳስ ዳዊት ፍቃዱ ነፃ ሆኖ አግኝቶ በግንባሩ ቢሞክረውም ፍሬው መልሶበታል ።

ከአንድ ደቂቃ በኋላ ድሬደዋ ከተማዎች በፈጣን እንቅስቃሴ ወደ ፊት በመጓዝ ከቀኝ መስመር ላይ እንየው ካሳሁን ያሻገረውን ኳስ ማማዱ ሲዲቤ በግንባር ገጭቶ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጠረ ።

ከግቡ መቆጠር በኋላ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት ወደ ፊት ጫና ለመፍጠር ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን ጅማ አባጅፋሮች የሚገኙ ኳሶችን በመልሶ ማጥቃት በፍጥነት ወደ ፊት ይዘው ቢሞክሩም ጠንካራ ሊባል የሚችል የግብ ሙከራዎችን ግን ማድረግ አልቻሉም ።

23ኛው ደቂቃ ላይ ድሬዳዋ ከተማዎች ያገኙትን ቅጣት ምት ሄኖክ ኢሳይያስ ከቀኝ መስመር ወደ ግብ ሲያሻማው ከተከላካዮች ሾልኮ የወጣው ሲዲቤ ኳሱን ጨርፎ ሁለተኛውን ግብ አስቆጠረ ። በግቦቹ ተነቃቅተው ጨዋታውን የቀጠሉት ድሬዎች 36ኛ ደቂቃ ላይ ሌላ ግብ አገኙ ። ከቀኝ መስመር የማዕዘን መምቻው አካባቢ የተገኘው የቅጣት ምት ሲሻማ የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋቾች በአግባቡ ማራቅ ባለመቻላቸው ኳሱ የደረሰው ማማዱ ሲዲቤ አስቆጠሮ ገና በ36 ደቂቃ ውስጥ ሶስታ መስራት ቻለ ። ይህም በ2014 የውድድር አመት ከፍቃዱ አለሙ ቀጥሎ ሶስታ መስራት የቻለ ሁለተኛው ተጫዋች እንዲሆን አስችሎታል ።

የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽም በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።

በሁለተኛው አጋማሽ ጅማ አባጅፋሮች ውጤቱን ለማጥበብ ቅያሪዎችን ገና በመጀመሪያው አጋማሽ ማድረግ ቢጀምሩም ወደ ፊት በመሄድ እና ለግብ የቀረበ ሙከራ በማድረግ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ ተቸግረው ነበር ።

ድሬደዋ ከተማዎችም የጥንቃቄ ጨዋታን የመረጡ በሚመስል መልኩ ከእረፍት በፊት ያገኙትን ውጤት አስጠብቀው ለመውጣት ጥረቶችን አድርገዋል ።

መደበኛው የጨዋታ ሰዓት ሊጠናቀቅ ሶስት ያህል ደቂቃዎች ሲቀሩት ተቀይሮ የገባ አድያሚን ናስር ለጅማ አባጅፋር የማስተዛዘኛዋን ግብ አስቆጠረ ። ጨዋታውም ሌላ ግብ ሳያክል በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።

በዚህም መሰረት የጨዋታው አሸናፊ ድሬዳዋ ከተማ ነጥቡን ወደ ስድስት ሲያሳድግ በአንፃሩ ጅማ አባ ጅፋር ያለ ምንም ነጥብ በደረጃው ግርጌ ላይ ቀጥሏል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...