መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ አሸንፏል
ሀዋሳ ከተማሰበታ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ አሸንፏል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተገናኙት ሀዋሳ ከተማ እና ሰበታ ከተማ ያደረጉት የሜዳ ላይ ፍልሚያ 1 ለ 0 ሲመሩ የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች የኋላ ኋላ ባስቆጠሯቸው 3 ግቦች ታግዘው ሙሉ 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል ።

ሁለቱም ክለቦች በስድስተኛ ሳምንት ጨዋታቸው ከተጠቀሙት ቋሙ አሰላለፍ ቅያሪዎችን አድርገው የገቡ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ በኩል 3 እንዲሁም በሰበታ ከተማ በኩል ደግሞ 5 ያህል ለውጦችን አድርገዋል ። በሀዋሳ ከተማ በኩል ዮሀንስ ሴጌቦ ፤ ወንድማገኝ ሀይሉ እና ዳዊት ታደሰ በሰበታ ከተማ በኩል ደግሞ አንተነህ ናደው ፤ ሀይለሚካኤል አደፍርስ ፤ዘላለም ኢሳይያስ ፤ ጁኒያስ ናንጄቦ እና ዱሬሳ ሹቢሳ ጨዋታውን መጀመር የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው ።

በጥሩ ፉክክር የተጀመረው ጨዋታ ቀስ በቀስ የኳስ ቁጥጥሩ ወደ ሰበታ ከተማዎች አድልቶ የተሻሉ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን አድርገው ገና በ10ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ግባቸውን አግኝተዋል ። ከቀኝ መስመር የተሻገረውን ዱሬሳ ሹቢሳ በግንባሩ በመግጨት ሰበታ ከተማን መሪ ያደረገ ግብ አስቆጠረ ።

 

ከግቡ መቆጠር በኋላ ሀዋሳ ከተማዎች መልስ ለመስጠት ሶስት ያህል ደቂቃዎች ብቻ ነበር የፈጁባቸው ። በ13ኛው ደቂቃ ላይ ከወንድማገኝ ሀይሉ የደረሰውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት የሞከረው ኤፍሬም አሻም በግብ ጠባቂው ቢመለስበትም የተመለሰውን ኳስ በድጋሚ አግኝቶ ግብ አድርጎታል ።

ከአቻነቷ ግብ በኋላ እንደ አጀማመራቸው መሆን ያልቻሉት ሰበታ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥሩ የተሻሉ ቢሆኑም የግብ ዕድሎችን በመፍጠሩ ረገድ በሀዋሳ ከተማ ብልጫ ተወስዶባቸው ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሊያስተናግዱ ችለዋል ። በዚህም 35ኛ ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር ወደ የተሻገረለትን ኳስ በግንባር በመግጨት ብሩክ በየነ ሀዋሳ ከተማን መሪ ያደረገ ግብ አስቆጠረ ።

ከመምራት ወደ መመራት የተቀየሩት ሰበታ ከተማዎች ቀደም ባሉት ደቂቃዎች ተሽለው ለመንቀሳቀስ የሞከሩ ሲሆን ከግቡ መቆጠር ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በሳሙኤል ሳሊሶ አማካኝነት ከቅጣት ምት ያደረጉት ሙከራ በግብ ጠባቂው ተመልሷል ። የመጀመሪያው አጋማሽመሰ በሀዋሳ ከተማ 2 ለ 1 መራነት ተጠናቀቀ ።

በተመሳሳይ ጥሩ የሜዳ ላይ ፉክክር የተጀመረው የሁለተኛው አጋማሽ ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ ሌላ ግብ አስተናገደ ። በቃሉ ገነነ ከቅጣት ምት ያሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ መስፍን ታፈሰ 52ኛ ደቂቃ ላይ የሀዋሳ ከተማን መሪነት ከፍ ያደረገ ግብ አስቆጠረ ።

በተቆጠሩባቸው ግቦች የተደናገጠለ የመሰሉት ሰበታ ከተማዎች ከሶስተኛው ግብ መቆጠር አምስት ደቂቃዎች በኋላ አምበላቸው በረከት ሳሙኤልን በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቶባቸዋል ። ይህም ጨዋታውይ ይበልጥ እንዲከብዳቸው ያደረገ ሲሆን በአንዳንድ አጋጣሚዎች በፈጣን ሽግግሮች ለመፍጠር የሞከሯቸው የግብ ዕድሎች ፍሬያማ ሊሆኑላቸው አልቻሉም ። ጨዋታውን በመምራት ላይ ያሉት ሀዋሳ ከተማዎች ጨዋታውን ተቆጣጥረው ከኋላ ተነስተው ያስቆጠሯቸወን ግቦች አስጠብቀው ጨዋታውን ማጠናቀቅ ችለዋል ።

በዚህም ሀዋሳ ከተማ ነጥቡን 10 በማድረስ ወደ 6ኛ ደረጃ ከፍ ሲሉ በአንፃሩ በውድድር አመቱ እስካሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው ሰበታ ከተማ በ4 ነጥብ ባለበት 15ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...