መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | የአዲስ አበባ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
ሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዲስአበባ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የአዲስ አበባ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ተደርጎ 2 – 2 በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ ለሀዋሳ ከተማ ብሩክ በየነ ሁለቱንም ግቦች ሲያስቆጥር ሪችሞንድ አዶንጎ እና ካሎጂ ሞንዲያ በራሱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ግቦችን አስቆጥረዋል ።

ሀዋሳ ከተማዎች በ23ኛው ሳምንት ከሰበታ ከተማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ላይ ከነበረው ምርጥ 11 አራት ለውጦችን በማድረግ አዲስአለም ተስፋዬ ፤ ዳዊት ታደሰ ፤ ወንድማገኝ ሀይሉን እና ብሩክ በየነን በላውረንስ ላርቴ ፤ አብዱልባሲጥ ከማል ፤ ሄኖክ ድልቢ እና አቤነዘር ኡቴ ምትክ ሲያሰልፉ በአዲስ አበባ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከወልቂጤ ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ቅያሪዎችን በማድረግ በዘሪሁን አንሼቦ ፤ ቴዎድሮስ ሀሙ ሮቤል ግርማ ምትክ ሳሙኤል አስፈሪ ፤ ልመንህ ታደሰ እና ፍራኦል መንግስቱን በቋሚነት አሰልፈዋል ።

 

ቀዝቀዝ ባለ እንቅስቃሴ የተጀመረው የቀትር 7 ሰዓቱ ጨዋታ በ7ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ቀዳሚውን ግብ ያስመለከተን ። ለአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ፍራኦል መንግስቱ ከርቀት ለሪችሞንድ አዶንጎ ለማቀበሌ የላከውን ኳስ የሀዋሳ ከተማው ተከላካይ ካሎንጂ ሞንድያ በግንባር ገጬቶ በራሱ መረብ ላይ አሳርፎታል ። ተጫዋቹም 15 ደቂቃዎችን በሜዳ ላይ ካሳለፈ በኋላ በአቤኔዘር ኡቴ ተቀይሮ ወጥቷል ።

ቀድመው ግብ ያስቆሩት አዲስ አበባ ከተማዎች በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይም ወደ ሀዋሳ ከተማ የግብ ክልል በመድረስ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠስ ችለዋል ።


ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረቶችን በማድረግ ላይ የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች ቀድሞ ከነበራቸው በተሻለ የአዲስ አበባ ከተሣ የኋላ መስመረን ለመፈተን የሞከሩ ሲሆን በዚህም በ31ኛው ደቂቃ ላየሰ የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችለዋል ። በወንድማገኝ ሀይሎ ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምተ ብሩክ በየነ በማስቆጠር የጨዋታውን ውጤት ወደ 1 – 1 መቀየር ችሏል።

በ38ኛው ደቂቃ ላይ ፍፁም ጥላሁን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በመሀመድ አበራ ተቀይሮ የወጣ ሲሆን በአጋማሹ የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ በሁለቱም በኩል ለግብ የቀሩቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዎ ነበር ።

በ42ኛው ደቂቃ ላይ ኤፍሬም አሻሞ ከሳጥኑ በቅርብ ርቀት የተገኘውን የቅጣት ምት አክርሮ ወደ ግብ ሞክሮ በዳንኤል ተሸሞ የተመለሰበት ሲሆኖ ከአንድ ደቂቃ በኋላም በአዲስ አበባ ከተማ በኩል ተቀይሮ የገባው መሀመድ አበራ ከሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ዕድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል ። የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ግብ ተጠናቀቀ ።

ጨዋታው ከእረፍት መልስ ከቀጠለ ሶስት ደቂቃዎች በኋላ ሀዋሳ ከተማዎች ከመመራት ወደ መምራት የተቀየሩበትን ግብ አስቆጥረዋል ። የመጀመሪያውን ግብ ያስቆጠረው ብሩክ በየነ ዳንኤል ደርቤ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ በዳንኤል ተሾመ መረብ ላይ በማሳረፍ ለራሱም ሆነ ለቡድኑ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል ።

ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ ተነቃቅተው ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ያደረጉት አዲስ አበባ ከተማዎች በ55ኛው ደቂቃ ላይ አቻ የሆኑበትን ግብ አግኝተዋል ። ግብ አስቆጣሪው ሪችሞንድ አዶንጎ ሲሆን ከቻርለስ ሪባኑ የደረሰውን ኳስ ተጠቅሞ ነበር የጨዋታውን ውጤት ወደ 2 – 2 የቀየረ ግብ ያስቆጠረው ። ግቡም ጋናዊውን አጥቂ በኮከብ ግብ አግቢነቱ ከአቡበከር ናስር እና ጌታነህ ከበደ ጋስ እኩል እንዲሆን አስችሎታል ።

ከግቦቹ በኋላ በኋላ በሁለቱም በኩል ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ የግብ ሙከራዎችን በማምከኑ ረገድ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ዳግም ተፈራ ድንቅ ብቃትን ማሳየት ችሏል ።

በ58ኛው ደቂቃ ላዬ ብሩክ በየነ ከወንድማገኝ ሀይሉ በግሩም ሁኔታ የደረሰውን ኳስ ሳይጠቀምበት ቀረ እንጂ ቡድኑንም ዳግም መሪ ለራሱም ደግሞ ሃትትሪክ የሚሰራበት አጋጣሚ ነበር ።

በ71ኛው ደቂቃ ላይ ሪችሞንድ አዶንጎ ያደረገውን ጠንካራ የግብ ሙከራ ዳግም ተፈራ አድኖበታል ። ከአራት ደቂቃዎች በኋላ አዲስአለም ተስፋዬ በሳጠረን ውሰጥ በሪችሞንድ አዶንጎ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ አዶንጎ መምታት ቢችልም ዳግም ተፈራ ሁለት ጊዜ መልሶበታል ።

በቀጣዮቹ የጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ አዲስ አበባ ከተማዎች በተሻለ ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረስ የቻሉ ሲሆን በ86ኛው ደቂቃ ላይ ቢንያም ጌታቸው ከሳጥን ውጪ ዘደ ግብ ሞክሮ ዳግም ተፈራ ያዳነበት ኳስ ለመዲናዋ ክለብ አስቆጪ ነበር ።

በመጨረሻም ጨዋታው በሁለት አቻ ውጤት ፍፃሜውን አግኝቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ ከተማ 35 አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ 23 ነጥብ ላይ የደረሱ ሲሆን ደረጃቸው ግን በነበሩበት 4ኛ እና 14ኛ ደረጃ የሚቀጥል ይሆናል ።

በ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ግንቦት 9 ረፋድ 4:00 ላይ አዲስ አበባ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን ሲገጥም በዕለቱ ቀን 10:00 ላይ ሀዋሳ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ጨዋታወን ያደርጋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...