መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን በመርታት ደረጃውን አሻሽሏል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን በመርታት ደረጃውን አሻሽሏል

አጋራ
አጋራ

በ14ኛው ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ በቀዳሚነት የተደረገው የድሬዳዋ ከተማ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ ቢጠናቀቅም በሁለተኛው አጋማሽ በተቆጠሩ ግቦች አዳማ ከተማዎች 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ።

ድሬዳዋ ከተማ በ13ኛው ሳምንት ከባህርዳር ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የነበረውን ቋመ አሰላለፍ ምንም ሳይቀይሩ የገቡ ሲሆን በአዳማ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ በመከላከያ በተሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶሰት ለውጦችን ያደረጉ ሲሆን ሚሊዮን ሰለሞን ፣ ዘካርያስ ከበደ እና ዳዋ ሆቴሳ ዮናስ ገረመውን ፣ አቡበከር ወንድሙን እና አብዲሳ ጀማልን ተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል ።በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በሁለቱም በኩል በተለያዩ አማራጮች ወደ ተቃራኒ የግብ ለመድረስ ጥረቶችን ያደረጉበት ነበር ። ድሬዳዋ ከተማ በተወሰነ መልኩ ኳሱይ ይዘው በመጫወት ወደ አዳማ ከተማ ግብ ለመቅረብ ሲሞክሩ በአዳማ ከተማ በኩል ደግሞ የፊት መስመር ተጫዋቾቻቸውን ዳዋ ሆቴሳን እና አሜ መሀመድን ኢላማ ያደረጉ ፈጣን ኳሶች ወደ ድሬዳዋ የግብ ክልል በማድረስ ጥሩ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችለው ነበር ።

በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃ ላይ በአዳማ ከተማ በኩል ዳዋ ሆቴሳ ለአሜ መሀመድ ጥሩ ኳስ ሰንጥቆለት አሜ ከግብ ጠባቂው ጋር ቢገናኘም የመስመር ዳኛው ከጨዋታ ውጪ ብለው አስቁመውታል ። ነገር ግን አጥቂው ከጨዋታ ውጪ አልነበረም ። በድሬዳዋ ከተማ በኩል ወደ አዳማ ከተማ የግብ ክልል መድረስ የቻሉባቸውን አጋጣሚዎች የፈጠሩ ቢሆንም ተከላካዮችን አልፎ ግብ ጠባቂውን የፈተነ ሙከራ ማድረግ ከብዷቸው ተስተውሏል ።በጨዋታው 4ኛ እና 15ኛ ደቂቃዎች ላይ ዳንኤል ሀይሉ ከሳጥኑ ውጪ ወደ ግብ ያደረጋቸው ሙከራዎች የመጀመሪያው ወደ ውጪ ሲወጣ ሁለተኛው ደግሞ በግብ ጠባቂው በጀማል ጣሰው ተይዞበታል ። በ23ኛው ደቂቃ ላይ መሀመድ አብዱልጢፍ የአዳማ ተከላካዮች ለመቀባበል ሲሞክሩ የነጠቀውን ኳስ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት ኳሱ ኢላማውን የጠበቀ ባለመሆኑ ሳይሳካ ቀርቷል ።

ከውሀ እረፍት መልስ ኳሱን የጀመሩት አዳማ ከተማዎች 27ኛው ደቂቃ ጥሩ የማግባት ዕድልን መፍጠር ችለው ነበር ። በአጋጣሚው አሜ መሀመድ ከአማኑኤል ጎበና የደረሰውን ኳስ ወደ ሳጥን ይዞ በመግባት ወደ ግብ የላከው ኳስ ዳዋ ሆቴሳ ተንሸራቶ ለማግኘት ቢጥርም ኳሱን ማግኘት ሳየችል ወደ ውጪ ወቷል ። በፈጣን ኳሶች ወደ ፊት በመድረስ የግብ ዕድሎችን በማግኘት ላይ የነበሩት አዳማ ከተማዎች 40ኛው ደቂቃ ላይም በጥሩ ቅብብል ወደ ፊት ያለፈ ኳስ አሜ መሀመድ ይዞ ወደ ሳጥን ገብቶ የሞከረው ኳስ ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን ሲጨርፈው የግቡን ቋሚ ለትሞ ወደ ውጪ ወቷል ። የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ምንም ግብ ተጠናቀቀ ።

በሁለተኛው አጋማሽ ድሬዳዋ ከተማዎች በመጀመሪያ አጋማሽ እንደነበረው ኳሱን ይዘው በመጫወት ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረስ የቻሉ ሲሆን በተለይም ከመስመር በሚነሱ ኳሶች ግብ ለማስቆጠር ጥረት አድርገዋል ። በአዳማ ከተማ በኩል ደግሞ በፈጣንን ሽግግሮች ወደ ፊት በሚልኳቸው ኳሶች ግቦችን ለማግኘት ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በዚህም ፍሬያማ መሆን ችለዋል ።

53ኛው ደቂቃው መሀመድ አብዱለጢፍ ከሙኽዲን ሙሳ ጥሩ ኳስ ደርሶት የነበረ ቢሆንም የአዳማ ከተማው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው ወጥቶ መልሶበታል ። 60ኛው ደቂቃ ላይ ረጃጅም ኳሶችን ወደ ፊት በተደጋጋሚ ያደርሱ የነበሩት አዳማ ከተማዎች ቀዳሚ የሆኑበትን ግብ አስቆጥረዋል ። ግቡን ያስቆጠረው የቡድኑ አምበል ዳዋ ሆቴሳ ሲሆን በረጅም የተላከለትን ኳስ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተከትሎ በቀጥታ ወደ ግብ የላከው ኳስ ከመረብ ጋር ተዋህዷል ።በ64ኛው ደቂቃ ላይ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ሄኖክ ኢሳይያስ ከቅጣት ምት ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ የቡድኑ ተጫዋቾች ከፊት በርከት ብለው ቢገኙም ኳሱን ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል ። ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ አዳማ ከተማዎች በቀኝ በኩል ያገኙትን የእጅ ውርወራ ጀሚል ያዕቆብ ሲወረውረው የደረሰው አሜ መሃመድ በፍጥነት ወደ ግብ በመድረስ አስቆጥሮ የአዳማ ከተማ መሪነትን ወደ 2 ለ 0 ከፍ አደረገ ።በሁለት ግብ ልዩነት በመመራት ላይ የነበሩት ድሬደዋ ከተማዎች 75ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ግባቸውን አግኝተዋል ። በዚህ አጋጣሚ ጋዲሳ መብራቴ ያሻገረውን ኳስ ጀማል ጣሰው ወጥቶ ለመያዝ ሲሞክር በሚገባ መቆጣጠር ሳይችል ኳሱ የሚሊዮን ሰለሞንን ጀርባ መትቶ ሲመለስ ያገኘው ዳንኤል ደምሴ ግብ አድርጎታል ። ከግቡ በኋላ ድሬዳዋ ከተማዎች ወደ ፊት ተጭነው መጫወት ሲሞክሩ አዳማ ከተማዎች ደግሞ ቀደም ብሎ ሳያደርጉት እንደነበረው በረጃጅም ኳሶች ሌላ ግብ ለማግኘት ሞክረዋል ።በዚህም 82ኛ ደቂቃ ላይ በፈጣን እንቅስቃሴ ተቀይሮ የገባው አቡበከር ወንድሙ ከዳዋ ሆቴሳ የደረሰው ኳስ በጥሩ አጨራረስ አስቆጥሮ ድሬደዋ ከተማዎችን ተስፋ ማስቆረጥ ችሏል ። ከአራት ደቂቃዎች በኋላም ዳዋ ሆቴሳ በረጅም የተላከለትን ኳስ ለማግኝት ሲጥር ከግቡ ለቆ የወጣው ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን ከሳጥኑ ውጪ በእጁ በመመለሱ በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ። በመጨረሻም ጨዋታው በአዳማ ከተማ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል ።ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ ነጥቡን 20 በማድረስ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ በ16 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

በ15ኛው ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ፋሲል ከተማን አዳማ ከተማ ደግሞ ሀዋሳ ከተማን የሚገጥሙ ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...