መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና ባሕር ዳር ከተማ በአንተነህ ተፈራ ግብ ሀዲያ ሆሳዕናን ረታ
ሀዲያ ሆሳዕናባህርዳር ከተማየጨዋታ ዘገባ

ባሕር ዳር ከተማ በአንተነህ ተፈራ ግብ ሀዲያ ሆሳዕናን ረታ

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1ለ0 በማሸነፍ ከሜዳው ውጪ ሦስት ነጥቦችን አሳክቷል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሀዲያ ሆሳዕና ግልጽ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ተቸግሮ በታየበት ጨዋታ፣ ባሕር ዳር ከተማ በ44ኛው ደቂቃ አንተነህ ተፈራ ከአሥራት ቱንጆ የተቀበለውን ኳስ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ አድርጓል። አጋማሹም በእንግዳው ቡድን 1ለ0 መሪነት ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ ሁለቱ ቡድኖች የተመጣጠነ ፉክክር ቢያደርጉም፣ ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በባሕር ዳር ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም ባሕር ዳር ከተማ በአንተነህ ተፈራ ወሳኝ ግብ ሦስት ነጥቦችን ሲያሳካ፣ ሀዲያ ሆሳዕና በሜዳው ያለ ነጥብ ቀርቷል።

የሙሉ ሰዓት ውጤት፦ ሀዲያ ሆሳዕና 0–1 ባሕር ዳር ከተማ

⚽️ 44′ — አንተነህ ተፈራ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...

አዳማ ከተማኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮጵያ ቡናና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ!

በአቤኔዘር አበበ ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ...