መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋር ከሶስት ተጫዋቾቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

ጅማ አባጅፋር ከሶስት ተጫዋቾቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

አጋራ
አጋራ

በ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለይም በመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ላይ በከፍተኛ የውጤት ቀውስ ውሰጥ ገብቶ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ለበርካታ ሳምንታት ተቀምጦ የቆየው ጅማ አባጅፋር ከ10ኛ ሳምንት በኋላ ድሬዳዋ ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ጥሩ መነቃቃት በማሳየት ነጥቦችን መሰብሰቡ ይታወቃል ።

በሊጉ ለመተረፍ በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ነጥቦችን መሰብሰብ የግድ የሚለው ክለቡም በተከፈተው የዝውውር መስኮት ላይ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ዛሬ በተሰማው መረጃ ደግሞ በክረምቱ ካስፈረማቸው ሶሰት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል ።

የመጀመሪያው የግራ መስመር ተከላካዩ አስናቀ ሞገስ ሲሆን የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ቡድን ከመቀላቀሉ በፊት በደደቢት ፤ ኢትዮጵያ ቡና ፤ ባህርዳር ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫውቶ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ ከአስናቀ ጋር በተመሳሳይ ቦታ ላይ የሚጫወተው እና ጅማ አባጅፋርን ከመቀላቀሉ በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህርዳር ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው ሚኪያስ ግርማ ነው ። ከዚህ ቀደም በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፤ ሜታ ቢራ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ ሀዋሳ ከተማ ፤ ኢትዮጵያ ቡና እና በድጋሚ በኢትዮ ኤሌክትሪክ የግብ ዘብ ሆኖ ካገለገለ በኋላ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቶ የነበረው ዮሀንስ በዛብህ ሶስተኛው ከክለቡ ጋር የተለያየው ተጫዋች ነው ።

ጅማ አባጅፋር የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን በነገው ዕለት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 4ኛ ላይ ከሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ጋር የሚያደርግ ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...