አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጅማ አባጅፋርን በቃኝ አለ

-አሰልጣኙ በዚህ ሰአት አዲስ አበባ አቧሬ ታቦታትን እየሸኘ ነው

-ከኢት.ቡና ጋር ያለውን ጨዋታ አይመራም

የጅማ አባጅፋሩ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ያለ ደመወዝ መስራቴ ይብቃ ብሎ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

የፊርማ ክፍያ ግማሹ ወደ 500ሺብር እንዲሁም ይ7ወር ደመወዝ እንዳልተከፈለው በመግለጽ ለክለቡ ደብዳቤ አስገብቶ አዲስ አበባ ተመልሷል።


ለክለቡ በጻፈውና በግልባጭ ለከንቲባ ጽ/ቤት፣ ለደጋፊ ማህበሩ፣ ለሊግ ካምፓኒ በግልባጭ በደረሰው ደብዳቤ የፊርማ ክፍያና ደመወዙ ካልተከፈለው ሀሙስ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከሚደረገው ጨዋታ ጀምሮ ከቡድኑ ጋር እንደማይቀጥል አሳውቋል።

ጅማ አባ ጅፋር በደመወዝ ክፍያና በውጤት እጦት እየታመሰ ሲሆን በሊጉ በ3 ነጥብና 9የግብ ዕዳ የመጨረሻውን 13ኛ ደረጃ መያዙ ታውቋል። ክክለቡ አመራሮች መሃል አንዱ ወደሆኑት አቶ አጃኢብ አባሜጫ የግል ስልክ ብደውልም ባለማንሳታቸውጭበዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን የክለቡን አቋም ማወቅ አልተቻለም

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport