በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርከት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት አባጅፋሮች በዛሬው ዕለት ደግሞ እያሱ ለገሰን ከአዲስ አበባ ከተማ ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
የዉድድር አመቱን በአዲስአበባ ከተማ ያሳለፈዉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ እያሱ ለገሰ ክለቡ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያድግ በግሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ በሁለት አመት የስምምነት ዉል ወደ ጅማ አባጅፋር ማምራቱ ታዉቋል።
አስተያየት ይስጡ