መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና “በትልቅ አሰልጣኝ ስር ለመስራት በመቻሌ እድለኝነት ይሰማኛል” ዱላ ሙላቱ /ሀዲያ ሆሳዕና/
ሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“በትልቅ አሰልጣኝ ስር ለመስራት በመቻሌ እድለኝነት ይሰማኛል” ዱላ ሙላቱ /ሀዲያ ሆሳዕና/

አጋራ
አጋራ

“ክለባችን ትልቅ ክለብ ነው ጥሩ የቡድን ስብስብ መያዛችን በአመቺው የባህርዳር ስታዲየም ላይ ከጅማ የበለጠ ውጤትን ይዘን እንድንመለስ ሰፊ ድርሻን ይጫወታል ።”

“በትልቅ አሰልጣኝ ስር ለመስራት በመቻሌ እድለኝነት ይሰማኛል” ዱላ ሙላቱ /ሀዲያ ሆሳዕና/


በሀድያ ሆሳዕና ጠንካራ የሊጉ ጉዞ ላይ ከመስመር እየተነሳ ቁልፍ ሚናን በመጫወት ለቡድኑ ወሳኝ ነጥቦችን በማስገኘት ላይ ይገኛል ።

ዱላ ሙላቱ በተለይም በአዳማ ቤት ያሰለጠኑትን አሸናፊ በቀለን በመከተል ወደ ሀድያ ሆሳዕና ካቀና በኋላ ቡድኑ በሚቸገርባቸው ወቅቶች ተቀይሮ በገባባቸው የጨዋታ መርሐ ግብሮች ለቡድኑ ውጤት የበኩሉን ሲወጣ ቆይቷል ።

ዱላ ሙላቱ ከ ሀትሪክ ስፖርቱ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር  ቆይታን ሲያደርግ የጅማ ቆይታቸውን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን አንስቷል ።

ስለ ጅማ ቆይታቸው . . . . . .

“በጅማ ቆይታችን ውጤታችን ትንሽ ተቀዛቅዞ የነበረበት መንገድ አንደኛው በርካታ ተጫዋቾቻችን በምግብ መመረዝ ታመውብን ነበር ። በሌሎች የጨዋታ ሳምንታት ላይ ይህ ሂደት የነበረ ሲሆን ታመውም ወደ ሜዳ የገቡ ተጫዋቾች ነበሩ ። እንደዛም ሆነ ውጤቱ ቢቀዘቅዝም ከነበሩብን ሁኔታዎች ውጤታችን ብዙም አስከፊ አልነበረም ።

ለሁለት ቀንም ቢሆን በጅማ ቆይታችን በመጠኑም ቢሆን መጉላላቶች ደርሰውብን ነበር ። ላረፍንበት ሆቴል ባለቤት በጊዜው ክፍያ ባለመፈፀሙ ምክንያት ሁለት ቀናትን በእግር በመጓዝ ሌላ ቦታ ለመመገብ ተገደን ነበር ። ደሞዝ ይገለፅ እንደነበረው ዘግይቷል ይህም የሆነው ስራ አስፈፃሚ የሽግግር ጊዜ ላይ በመሆኑ ሲሆን እስከ አሁንም ክፍያ አልተፈፀመልንም ።”

ተቀይሮ በመግባት ስለሚያሳየው ብቃት . . . .

“ሁሌም ተቀይሬ ስገባ አንድ ነገር ይዤ መውጣት እንዳለብኝ እረዳለሁ ፣ ሁሌም ወደ ሜዳ ስገባ በንፁህ አእምሮ እና በጎ ነገር እሰራለሁ ብዬ ስለምገባ እየተሳካልኝ ነው ። ማንም ተጫዋች ተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጥን አይወድም ። ሆኖም ግን የሚያስቀምጡክ አስገዳጅ ሆኔታዎች ይኖራሉ ፣ ነግር ግን በተሰጡክ እድሎች ያለህን ነገር አድርገህ ጥሩ ነገር ለመስራት ሁሌም ወደ ሜዳ መገባት እንዳለበት ይሰማኛል ።”

ሀድያ ሆሳዕና ባህር ዳር ላይ . . . .

“የባህርዳር ቀጣይ ጨዋታዎች መልካም ይሆናሉ ብዬ አምናለሁ ። ቢያንስ ጅማ ላይ የያዝናቸው ውጤቶች ባህርዳር ላይ ይኖራሉ ብዬ አላስብም የተሻለ ውጤት እንደሚኖረን አስባለው ። ክለባችን ትልቅ ክለብ ነው ጥሩ የቡድን ስብስብ መያዛችን በአመቺው የባህርዳር ስታዲየም ላይ ከጅማ የበለጠ ውጤትን ይዘን እንድንመለስ ሰፊ ድርሻን ይጫወታል ።”


ዱላ ሙላቱ እና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ . . . . .

ከአሸናፊ በቀለ ጋር መስራት በመቻሌ ሁሌም ደስተኛ ነኝ ፣ እሱ ትልቅ አሰልጣኝ ነው ። ሁሌም ከእርሱ ጋር በምሰራባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ደስተኛ ነኝ ። በትልቅ አሰልጣኝ ስር ለመስራት በመቻሌ እድለኝነት ይሰማኛል ፣ ከእርሱ ብዙ ነገሮችን እየተማርኩ እገኛለው ።

ዱላ ሙላቱ በዘንድሮው የውድድር ዓመት . . . . .

በዘንድሮው የውድድር ዓመት የእኔ ትልቁ ምኞቴ የተሻለ ተጫዋች መሆን ፣ ጎሎችን ማስቆጠር ፣ የተሻለ ነገርን ሰርቶ ማጠናቀቅ ቡድኔን ማገዝ ፣ ሁሌም ወደ ሜዳ ስገባ የተሻለ ነገርን መስራት ፣ ከእኔ የሚጠበቀውን ነገር ማድረግ ቢሆኑም ከሁሉም በላይ ግን የእኔ ትልቁ ግብ ቡድኔን በደረጃ ውስጥ ማስጨረስ ነው ።

አብሮት መጫወት ስለሚፈልገው ተጫዋች . . . .

የመስመር ተጫዋች ስትሆን የመሀል ሜዳ ተጫዋችን ትመርጣለክ ፣ እኔም ከ ብሩክ ቃልቦሬ ጋር ስጫወት በጣም ደስ ይለኛል ምክንያቴ ደግሞ ከእርሱ ጋር ሁለት አመታትን መጫወት ችያለው በእነዚህ ሁሉ ጊዜ አብሬው ስጫወት ምቾት ይሰማኛል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...