ያለፉትን አመታት በአውሮፓ ሊጎች ላይ በመጫወት ስኬታማ ጊዜያትን ሲያሳልፍ ለመመልከት ተችሏል ፣ ብዙ የሀገራችን ተጫዋቾች በሚያልሙት የክለቦች ውድድር የ ዩሮፓ ሊግ ላይ ተጫውቶ ሲያሳልፍ ለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በተሰለፈባቸው አጋጣሚዎች ቁልፍ ሚናን ሲጫወት ታይቷል ።
ከረጅም ጊዜ የአውሮፓ ቆይታ በኋላ ወደ ናፈቃት ሀገር ኢትዮጵያ ከመጣ ቀናትን ያስቆጠረው ቢንያም በላይ ከ ሀትሪክ ስፖርት ፀሀፊው ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን አድርጓል ።
ስለ ስዊድን ቆይታው . . . . . . . .
ህይወት በስዊድን በጣም ጥሩ ነበር ፈጣሪ ይመስገን ፣ በነበረኝ የአውሮፓ ቆይታማ ሶስት ዋንጫዎችን ከማሳካት ባለፈው በትልቁ የክለቦች የውድድር መድረክ ዩሮፓ ሊግ ተጫዋቼ አሳልፌያለው ።
ስለ አሁን ክለቡ ኡመያ እና ቀጣይ ሂደቶች . . . . .
በ ኡመያ ክለብ ፊርማዬን አላራዘምኩም ፣ እስከ አሁን ከ ክለቡ ጋር ቤተሰብ ነን ። ከ ኡመያ ክለብ አመራሮች እና ደጋፊዎች ጋር ምንም አይነት ምክንያት የለም ፣ ነገሮች መልካም ከሄዱ እዛው ልቀጥል እችላለው ካልሆነም ፈጣሪ የፈቀደው ይሆናል ።
ስለ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ . . . . . .
የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን እከታተላለው በዚህ አመት መልካም የሆነ አጋጣሚ ነበር ። ውድድሮቹ በቴሌቪዥን ይተላለፉ ስለነበር ብዙዎቹን ጨዋታ የመመልከት እድል አግንቻለው ፣ ጥሩ ፉክክር እየታየበት ያለ ዉድድርም ሆኖ ለመመልከት ችያለው ።
ስለ ናፈቀው ነገር . . . . . .
በአውሮፓ ለረጅም ጊዜ እንደማሳለፌ እና መቆየቴ ቤተሰቦቼ እና ቤተክርስቲያ (ገዳማት) በጣም ናፍቀውኝ ነበር ።

የቢንያም በላይ ምኞት . . . . . .
ከ አውሮፓ የረጅም ጊዜ ተሞክሮዬ የሀገራችን ሊግ ቢኖረው ብዬበጣም ብዙ ነገሮች እመኛለው ….. ወደ ፊት የምመኛቸው ነገሮች ይስተካከላሉ ብዬ አስባለው ። በጣም ብዙ ተጫዋቾች አሉ አብሬያቸው ብጫወት ብዬ የምመኘው ጊዜ አይበቃንም መጥራት ከጀመርኩ ሀሀሀ
ስለ ብሔራዊ ቡድን . . . . . .
ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ” ውቤ ” ጋር ጥሩ ግንኙነት ነው ያለን ፣ በተጠራሁ ጊዜ ሀገሬን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ ።

ልዩ ቦታ ስለሚሰጣቸው አሰልጣኞች . . . . .
በብዙ አሰልጣኞች ስር እንደማለፌ ለሁሉም ክብር እና ፍቅር አለኝ እዮብ ተዋበ ከታች ጀምሮ ያሳደገኝ አሰልጣኝ ነው ፣ ጣሰው ታደሰ ፣ አሰልጣኝ ግርማ ፣ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም ፣ አሰልጣኝ ሲሳይ በዋናነት ደግሞ አሰልጣኝ ዮሀንስ ሰሀሌ ላመሰግነው እወዳለሁ እሱ በኔ የእግርኳስ ህይወት ውስጥ ያደረገው ነገር ተወርቶ አያልቅም ።
በመጨረሻም . . . . . .
በመጨረሻም የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን ቤተሰቦቼንም ከልቤ አመሰግናለሁ ። ያለነሱ እገዛ ከባድ ነበር ከጎኔ ሆነው እዚ ለመድረሴ እገዛ ላደረጉልኝ ሁሉ በፈጣሪ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ ።
አስተያየት ይስጡ