መነሻ ገጽ ቃለመጠይቅ ” አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደርሶኝ ከገባው በኋላ ለእግር ኳስ ስል (ዊዝድሮ) ሞልቼ ነው የወጣሁት “አሰጋኸኝ ጴጥሮስ /አዲስአበባ ከተማ/
ቃለመጠይቅቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዲስአበባ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

” አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደርሶኝ ከገባው በኋላ ለእግር ኳስ ስል (ዊዝድሮ) ሞልቼ ነው የወጣሁት “አሰጋኸኝ ጴጥሮስ /አዲስአበባ ከተማ/

አጋራ
አጋራ

” አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደርሶኝ ከገባው በኋላ ለእግር ኳስ ስል (ዊዝድሮ) ሞልቼ ነው የወጣሁት “

” ከተቻለ ከታላቅ ወንድሜ ጋር በአንድ ክለብ መጫወት ካልሆነ ደግሞ እሱን በተቃራኒ መግጠም ምኞቴ ነው! …. “


በ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ጥሩ እንቅሰቃሴን በማሳየት ላይ ይገኛል ። ከዚህ ቀደም በብሄራዊ ሊግ እና በከፍተኛ ሊግ ለተለያዩ ክለቦች መጫወት ችሏል ። በዚህ የውድድር ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደጉት ሶስት ክለቦች አንዱ ለሆነው ለአዲስ አበባ ከተማ እየተጫወተ ያለው አስረሳኸኝ ጴጥሮስ ።

ስለእግር ኳስ ህይወቱ እና ሌሎች የግል ጉዳዮች ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ ጋር ቆይታ አድርጓል ።


ሀትሪክ:- በመጀመሪያ ራስህን አስተዋውቀኝ የተወለድክበትን ቦታ ፤ ለቤተሰብህ ስንተኛ ልጅ እንደሆንክ ?

አሰጋኸኝ:- እሺ አመሰግናለሁ ስሜ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ እባላለሁ የተወለድኩት አርባምንጭ ሲሆን በተለምዶው ልማት ሰፈር ይባላል … ለቤተሰቤ ሁለተኛ ልጅ ነኝ

ሀትሪክ:- ስለ እግር ኳስ አጀማመርህ አጫውተኝ እስቲ ?

አሰጋኸኝ:- ያው እግር ኳስን እንደማንኛውም ታዳጊ በ ፕሮጀክት ነው የጀመርኩት አንድ በራሱ ተነሳሽነት የሚያሰራን አብርሃም አንበሴ የሚባል ልጅ ነበር ከዛ በኋላ ሌላ ፕሮጀክት ገባው አንድ የስፖርት መምህር አለ መኳንንት ካስዬ ይባላል አሁን በህይወት የለም እሱ ነው ለትምህርት ቤት ስጫወት አይቶኝ አንድ ገረመው ተበጀ የሚባል አሰልጣኝ ወደሚያሰራበት ፕሮጀክት ያስገባኝ

ሀትሪክ:- ከፕሮጀክት በኋላስ ?

አሰጋኸኝ:- ከፕሮጀክቱ በኋላ እዛው ስሰራ ያየኝ ያአሁኑ የአርባምንጭ ከነማ ምክትል አሰልጣኝ ማትዮስ ለማ ለጋሞ ጨንቻ እንድጫወት ጠየቀኝ በሰዓቱ ጋሞ ጨንቻ ብሔራዊ ሊግ ለመግባት ፉላጎት ፍላጎት እንዳላቸው አወሩኝ ከዛም አሁን ባህርዳር ከነማ ከሚጫወተው አለልኝ አዘነ ጋር አንድ ላይ ጋሞ ጬንቻን ወደ ብሔራዊ ሊግ አስገባነው ። በዛ ውድድር ላይ ባሰየሁት እንቅስቃሴ ንግድ ባንክ ተስፋ ቡድን ልገባ ችያለሁ

ሀትሪክ:- ጋሞ ጨንቻን ወደ ብሔራዊ ሊግ ስታስገቡ የት ነበር ውድድሩ የተካሄደው ?

አሰጋኸኝ :-ውድድሩ አርባምንጭ ላይ በ2009 ነበር የተካሄደው

ሀትሪክ:- ከጋሞ ጬንቻ ወደ ንግድ ባንክ ተስፋ ቡድን ሄድክ ከዛ በኋላስ ?

አሰጋኸኝ :- ከዛ በኋላ ባንክ ፈረሰ እሰከ ውድድሩ ዓመቱ አጋማሽ በግል እሰራ ነበር ከግማሽ በኋላ ብሔራዊ ሊግ ለሚሳተፈው ጎፋ ባራንቼ ለሚባል ክለብ ፈረምኩ በመቀጠል ወደ ከፍተኛ ሊግ ለማደግ ማጠቃለያውን ስናልፍ በዛ ውድድር ላይ አሰልጣኝ ሻንበል መላኩ አይተውኝ ወሎ ኮምቦልቻን ተቀላቀልኩ በዛ ዓመት በ ኮቪድ-19 ምክንያት ውድድሩ እስኪቋረጥ ድረስ በምድባችን 2ኛ ነበርን ከዛ በሚቀጥለው ዓመት አዲስ አበባ ከተማን ተቀላቀልኩ

ሀትሪክ :- የአዲስ አበባ ከተማ ቆይታህ እንዴት ነው ?

አሰጋኸኝ :- የአዲስ አበባ ቆይታዬ በጣም ጥሩ ነው ከ አምና ጀምሮ በቡድኑ ውስጥ የመጀመሪያ ተሰላፊ ነኝ አምና ጎሎችን አስቆጥር ነበር ዘንድሮ ለሊጉም አዲስ ስለሆንኩ ጎሎችን ማስቆጠር አልቻልኩም ከዚህ በኋላ ግን ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኔን ለማገዝ ከፈጣሪ ጋር ጠንክሬ እሰራው ነው

ሀትሪክ :- ውድድሩን ስትጀምሩ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንገባለን ብላችሁ አስባችሁ ነበር ?

አሰጋኸኝ :- ውድድሩን ስንጀምር እንደዛ አስበን አልነበረም ምክንያቱም አብዛኛው የቡድናችን ልጆች ወጣቶች ነበርን ከዛ ጨዋታዎችን ማድረግ ስንጀምር ነው ቡድናችን በጣም አዝናኝ ኳስ የሚጫወት እና ቶሎ ቶሎ ጎሎችን ማስቆጠር ስንጀምር ክለቦችም ለእኛ ከፍተኛ ግምት እየሰጡ ሲመጡ መግባት እንዳለብን ተተሰማን ይሄ ነገር ደግሞ ለእኛ ትልቅ በራስ መተማመን ፈጥሮልን ነበር

ሀትሪክ:- ከስንተኛው ሳምንት በኋላ ነው መግባት አለብን ብላችሁ መጫወት የጀመራችሁት ?

አሰጋኸኝ:- የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ነው ተብሎ የሚታመነውን ነቀምት ከተማን 4-0 ስናሸንፍ ነው ለዋንጫ መጫወት እንዳለብን ያወራነው

ሀትሪክ:- ወደ ፕሪምየር ሊግ መግባታችሁን ስታረጋግጡ የነበራችሁን ስሜት አጋራን እስቲ ?

አሰጋኸኝ:- በጣም ደስ የሚል ስሜት ነበር ምክንያቱም በጊዜ ነው ያረጋገጥነው ሲቀጥል ቡድናችን በጣም በፍቅር የተሞላ ነበር ብቻ ደስታውን ለመግለጽ ይከብደኛል

ሀትሪክ:- ከሌሎች ቡድኖች ክለባቹ የሚለየው በአንድነታቹ ነበር ይሄ ከምን የመጣ ነው ?

አሰጋኸኝ:- አዎ ያ የመጣው አንድ አይነት እድሜ ላይ መሆናችንም ነው በዛ ላይ የተወሰኑ ሲኒየሮችም ነበሩ እነሱም በጣም ያግዙን ነበር ብቻ ያለው አንድነት በጣም ደስ ይል ነበር ሁሉም መጫወት አለመጫወቱን ሳይሆን የቡድኑን ውጤት ነበር የሚያስቀድሙት

ሀትሪክ:- በእግር ኳስ ይህወትህ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስትጫወት የመጀመሪያህ ነው ምን ስሜት ፈጠረብህ ?

አሰጋኸኝ:- በጣም ደስ የሚል ስሜት ነበር የፈጠረብኝ ምክንያቱም የልጅነት ህልሜ ነበር

ሀትሪክ:- ገና ወጣት ነህ በዚህ እድሜህ በቋሚነት እየተጫወትክ ነው ጠንክረህ የመስራትህ ውጤት ነው ማለት እንችላለን ?

አሰጋኸኝ:- አዎ ምክንያቱም ወደ እኛ አከባቢ በስራ ነው የሚታመነው ታላላቆቻችን ጠንክረው ሰርተው የደረሱበትን ስላየው እኔንም ጠንካራ ሰራተኛ ያደረገኝ እሱ ነው

ሀትሪክ:- በሊጉ ጅማሬያቹ ጥሩ አልነበረም ምክንያቱ ምንድነው ?

አሰጋኸኝ:- አዎ በሊጉ አጀማመራችን ጥሩ አልነበረም ምክንያት ነው ብዬ የማስበው የዝግጅት ግዜ ማጠር ነው ሲቲ ካፕ እራሱ 10 ቀን ሰርተን ነው የተሳተፍነው

ሀትሪክ:- ከዛ በኋላስ ?

አሰጋኸኝ:- ከዛ በኋላ ያው ችግራችን ላይ እየሰራን በአጋጣሚ ብሔራዊው ቡድናችን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ነበረበት በዚህ ምክንያት በተሰጠው የእረፍት ጊዜ እኛ ወደ እረፍት ሳይሆን ማስተካከል ባሉብን ነገሮች ላይ ነው ስንሰራ የቆየነው

ሀትሪክ:- ከእረፍት መልስ የአሰልጣኝ ለውጥ አድርጋችሁ ነው ወደ ድል የተመለሳችሁት ?

አሰጋኸኝ:- አዎ ግን ያው በነበረው ነገር እንጂ የተቀየረ ነገር አልነበረውም

ሀትሪክ:- ስለ ብሔራዊ ቡድናችን ምን ትላለክ ?

አሰጋኸኝ:- ብሔራዊ ብድናችን በጣም ጥሩ ኳስ የሚጫወት ነው በዚህ ሰዓት የተሻለ ስብስብ አለን እና በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሻለ ነገር እንጠብቃለን

ሀትሪክ:- ለብሔራዊ ቡድን የመጫወት ህልምህ ?

አሰጋኸኝ:- እንደማንኛውም ተጫዋች ሀገሬን ወክዬ መጫወት እፈልጋለሁ ከፈጣሪ ጋር በቅርቡ አሳካለሁ ብዬ አስባለሁ

ሀትሪክ:- በሀገር ውስጥ ማንን እያየክ ነው ያደከው ?

አሰጋኸኝ:- አበባው ቡጣቆ እና ታላቅ ወንድሜን ምንያምር ጴጥሮስን ነው ከልጅነቴ ጀምሮ እያየው ያደኩት

ሀትሪክ:- ከአበባው ቡጣቆ ጋር በተቃራኒነት ገጥመኻል ስሜቱ እንዴት ነበር ?

አሰጋኸኝ:- በጣም ለብዙ ሰው ግርምትን የፈጠረ ነገር ነበር ምክንያቱም እሱ ሲጫወት እኔ ገና ልጅ ነበርኩ ፕሮጀክት እንኳን አልገባውም ነበር እሱ ነበር በብዙ ነገር የሚያግዘኝ ከትጥቅ ጀምሮ…።

ሀትሪክ:- ስለዚህ አበባው ቡጣቆ በእግር ኳስ ህይወትህ ትልቅ አሻራ አሳርፏል ማለት ይቻላል ?

አሰጋኸኝ:- አው በጣም ከሚባለው በላይ ለእኔም ለታላቅ ወንድሜም በዚህ አጋጣሚ በጣም ላመሰግነው እፈልጋለሁ በዚህ አጋጣሚ ወንድሜ ነው ተለያይተን የምናሳልፈው ጊዜም የለም

ሀትሪክ:- ከውጭ ሀገር ተጫዋቾች ማነው አርአያክ ?

አሰጋኸኝ:- የዳኒ አልቬዝ አጨዋወት አድናቂ ነኝ አርአያዬ ግን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው

ሀትሪክ:- እግር ኳስ ተጫዋች ባትሆንስ ?

አሰጋኸኝ:- እግር ኳስ ተጫዋች ባልሆን በትምህርቴ እቀጥል ነበር አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደርሶኝ ከገባው በኋላ ለእግር ኳስ ስል ዊዝድሮ ሞልቼ ነው የወጣሁት

ሀትሪክ:- የእረፍት ጊዜህን እንዴት ነው የምታሳልፈው ?

አሰጋኸኝ:- የእረፍት ጊዜዬን የእምነት ቦታዎችን በመሳለም እና የተለያዩ ፊልሞችን በማየት ነው የማሳልፈው

ሀትሪክ:- የቡድናቹ አዝናኙ ልጅ ማነው ?

አሰጋኸኝ:- አምና በጣም ያዝናናን የነበረው ተክሉ ተስፋዬ ነበር አሁን ላይ ብዙም የለም

ሀትሪክ:- ዘናጩስ ተጫዋች ?

አሰጋኸኝ:- እያሱ ለገሰ አላባ ነው

ሀትሪክ:- የወደፊት ምኞትህ ?

አሰጋኸኝ:- የወደፊት ምኞቴ ከተቻለ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከታላቅ ወንድሜ ጋር በአንድ ክለብ መጫወት ነው ካልሆነ ደግሞ እሱን በተቃራኒ መግጠም ምኞቴ ነው በዚህ በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደረ ለሚገኘው ሀምበሪቾ ዱራሜ እየተጫወተ ይገኛል ያለፈውን አመት ደግሞ ለድሬ ዳዋ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል

ሀትሪክ:- በመጨረሻ ማመስገን የምትፈልጋቸውን ሰዎች ማመስገን ትችላለክ ?

አሰጋኸኝ:- ማመስገን የምፈልገው በመጀመሪያ የድንግል ማሪያም ልጅ መድሀኒዓለም የተመሰገነ ይሁን ሲቀጥል ደሞ ወላጅ እናቴ አበራሽ ከበደ በመቀጠል ደሞ ከራሱ በላይ ለኔ ብዙ ነገሩን የሰጠው ታላቅ ወንድሜ ለሱ ቃላት የለኝም ምንያምር ጴጥሮስ … ሙሉ የአዲስ አበባ ከነማ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ስታፍ ማመስገን እፈልጋለሁ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...