ሀድያ ሆሳዕና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሲሾም የናትናኤል ሞገስን ውል አራዝሟል።

በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እየተመሩ የቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናክረው የቀጠሉት ሀድያ ሆሳዕናዎች የቀድሞው የአዳማ እና ፋሲል ከነማ ተጫዋች እንዲሁም ለሦስት አስርት አመታት በፋሲል ከነማ በምክትል እና በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ያሳለፈው አዳም ባዘዘው የነብሮቹ ግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ሲሾም ከወጣት ቡድኑ የተገኘው የግራ መስመር ተከላካዩ ናትናኤል ሞገስ በክለቡ ውሉ ተራዝሞለታል።
አስተያየት ይስጡ