ሀላባ ከተማ ዝግጅት የሚጀምረው የመጨረሻው ክለብ ሆኗል

ከከፍተኛ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ በማደግ በ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው ሀላባ ከተማ ከአሳዳጊ አሰልጣኙ በሽር አብደላ ጋር እንደማይቀጥል በመታወቁ የቀድሞው አሰልጣኙ ካሊድ መሐመድን በይፋ መቅጠሩ የሚታወስ ሲሆን አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ከመቀላቀል ባሻገር ውላቸው የተጠናቀቁ ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝም የቆየ ሲሆን አሁን ዝግጅት ሊጀምር መሆኑን ደግሞ ክለቡ አሳውቋል።
የፊፋችን ቅዳሜ እና ዕሁድ የቡድኑ አባላት ከተሰባሰቡ በኋላ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው የፊታችን ሰኞ ነሐሴ 25/2018 እንደሚጀምሩ ክለቡ የላከልን መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ