በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና መሪነት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን አጠናክረው በመስራት ላይ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች ረዳት አሰልጣኝ ቀጥሯል።

ከዚህ ቀደም በካፋ ቡና የከፍተኛ ሊግ ቆይታን ማድረግ የቻለው እና በኢትዮጵያ መድን ከ20 አመት በታች እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ የአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ ረዳት በመሆን በመድን ያሳለፈው ሠለሞን ባየልኝ በቅርቡ ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር ከወሰደው የኤ ላይሰንስ ስልጠና በኋላ የሀዋሳ ከተማ ረዳት ሆኖ ተመርጧል።
አስተያየት ይስጡ