መነሻ ገጽ ሀላባ ከተማ ለተከታታይ አመት ስኬታማ የሆነውን አሰልጣኝ በሊጉ ላይ ልናየው ግድ ይላል
ሀላባ ከተማሀላባ ከነማዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለተከታታይ አመት ስኬታማ የሆነውን አሰልጣኝ በሊጉ ላይ ልናየው ግድ ይላል

አጋራ
አጋራ

ለተከታታይ አመት ወደ ፕሪምየር ሊግ ያሳደገው እና ሀላባ ከተማን የ2018 የከፍተኛ ሊጉ ቻምፒዮን ያደረገው በሽር አብደላ ማነው ?

አዲሱን ኮከብ አሰልጣኝ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ማየት አለን ብሎ በዕርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምን አልባት ለብዙዎች ትላንት የመጣ ሰው መስሎ ቢታይም እግር ኳስን በደንብ በመጫወት ጭምር ራሱን በሚገባ ያሳየ ተጫዋችም ጭምር እንጂ ፣ የተጫዋችነት ዘመኑን ከአንጋፋው ደደቢት ጀምሮ ለወልቂጤ ከተማ እና መቂ ከተማ እንዲሁም ደግሞ ተወልዶ ላደገበት ነገሌ አርሲ ጭምር በመጫወት ያሳለፈ ቢሆንም ለብዙ ተጫዋቾች መሰናክል በሆነው ጉዳት ግን በፈለገው ልክ የረዘመ ጉዞ እንዳይኖረው ሳንቃ ሆኖበታል።

ባስተናገደው ጉዳት በእግር ኳስ ተስፋን ቆርጦ በአንድ ወቅት ስደትን ምርጫው እስከ ማድረግ ደርሶ የነበረው የወቅቱ ስኬታማው ወጣት አሰልጣኝ ከውስጡ አልጠፋ ያለው የእግር ኳስ ልክፍት ወደ ተጫዋችነቱ ባይመልሰውም ሰፈር ውስጥ በማሰልጠን የጀመረው ጅምሩ ኢትዮጵያ ውስጥ በአጭር ጊዜ ስማቸውን ከፍ ካደረጉ አሰልጣኞች ተርታ አንዱ መሆን እንዲችል ጭምር እንዲገኝ አድርጎታል። በስንዴ እና ወተት ምርቶቿ ለሀገራችን በረከት ከሆነችው የትውልድ ከተማው ክለብ ነገሌ አርሲ ልክ የዛሬ ሰባት አመት በረዳት አሰልጣኝነት የክለብ የስልጠና አለምን ለመቀላቀል የበቃው አሰልጣኝ በሽር አብደላ ከረዳት አሰልጣኝነት በመነሳት ነገሌ አርሲን ከብዙ ፈተናዎች ጋር በዋና አሰልጣኝነት በመረከብ ቡድኑን በከፍተኛ ሊጉ ስሙ ገኖ እንዲወጣ ብቻም ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንዲታወቅ ጭምር ያስቻለ ሲሆን ነገሌ አርሲን ብቻም ሳይሆን አዳዲስ ወጣቶችን ጭምር እንካቹ በማለት የስኬት መደላድል ውስጥ በፍጥነት መገኘትም ችሏል።

ከነገሌ አርሲ በኋላ በ2017 የውድድር ዘመን ከተመሠረተ ሁለተኛ አመት የሞላውን ሸገር ከተማን ሁለተኛ ክለቡ አድርጎ በዋና አሰልጣኝነት በመረከብ በአንድ አመት ውስጥ ክለቡን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማሳደግ አመቱን ደግሞ በማጠቃለያ ውድድር ሁለተኛ ሆኖ እንዲፈፅም ለማድረግ የበቃው አሰልጣኙ በክለቡ የማይፋቅ ታሪክን ሰንዶ በጎመራ ልኬት አመቱን አጠናቋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በያዝነው የውድድር ዘመን እንደምንመለከተው ቢጠበቅም በድንገት በወጣው የፌድሬሽኑ የላይሰንስ መመሪያ የተነሳ በብዙ የጥረት ዋጋ ካሳደገው ክለብ ጋር ለመመልከት አልታደልንም።

ተስፋን ሳይቆርጥ አሁንም ከፍተኛ ሊጉ ላይ ማሰልጠኑን ምርጫው ከማድረግ ያልቦዘነው አሰልጣኙ የሀገሪቱን ትልቁን የሊግ ዕርከን ለዘመናት የተራበው ሀላባ ከተማን በመረከብ አመቱን በስኬት በማጠናቀቅ የአምናውን ታሪክ ለሁለተኛ ተከታታይ አመት መድገምም ችሏል። በእግር ኳስ ክህሎት በፍቅር ለናወዘው የበርበሬ መገኛዋ ሀላባ ከተማ አለሁ ብሎ በያዘበት አመት የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ አሸናፊ ሆኖ ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳደግ ብቻም ሳይሆን የሌላኛውን የምድብ ሀ አሸናፊ ጋሞ ጨንቻን በመለያ ምት በማሸነፍ ጭምር የውድድር ዘመኑን በዋንጫ አሟሽቶ በድል በሮች አልፎ ባለ ብዙ ተስፋው አሰልጣኝ ምን ያህል ከፍ ያለ የማሰልጠን አቅሙ ላይ እንዳለም ማለይ ይቻላል።

በመጨረሻም ሀሳቤን ሳሟሸው አሰልጣኝ በሽር በያዘው የC ላይሰንስ ከሸገር ከተማ ጋር በፕሪምየር ሊጉ መመልከትን ባንችልም አሁን እየወሰደ ካለው የB ላይሰንስ ስልጠናን ታሳቢም በማድረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በስኬት ላቆጠቆጡ ነገም ኢትዮጵያን ለሚጠቅሙ እንደ አሰልጣኝ በሽር አብደላ እና እንደ ጋሞ ጨንቻው ማቲዮስ ለማ አይነት ወጣት አሰልጣኞች እንደ ነገሌ አርሲው ቱሉ ደስታ ሁሉ በፕሪምየር ሊጉ የማሰልጠን ዕድልን ማመቻቸት አለበት የሚል እምነት አለን።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...